ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እድሳት የተደረገለት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተመረቀ

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ከ 30 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማውጣት ለመሰብሰቢያ አዳራሹ የእድሳት ስራን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፤ በዛሬው እለትም አዳራሹ ሙሉ ለሙሉ የእድሳቱ ስራ ተጠናቆ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና የብልፅግና ፖርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ይሱፍ በተገኙበት ተመርቋል።

በዚህም አዳራሹ ዘመናዊ ደረጃውን የጠበቀና ድሬዳዋን በሚመጥን መልኩ እንደተገነባ እንዲሁም ለእድሳቱ 6 ወራትን እንደፈጀ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን ተናግረዋል።

ዘመኑን ባማከለ መልኩ የስራ ቦታን መቀየር እንዲሁም የስራ ቦታን ምቹና ማራኪ ማድረግ ተገቢ መሆኑንም የገለፁት ክብርት አፈ ጉባኤዋ ምክር ቤቱ የወረቀት አሰራርን ወደ ዲጂታል መቀየሩንም ጠቁመዋል።

በመጨረሻም በቀጣይም እንደነዚህ አይነት ስራዎችን የማዘመን ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ክብርት ፈቲያ አመላክተዋል።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:-ቴድሮስ ልዑልሰገድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *