ልዩ መለያ ኮድ የተካተተበት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ የማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ

የደረሰኝ ህትመት አሰራር ሂደትን አስመልክቶ በትላንትናው እለት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የገቢ ዘርፍ አመራሮች ጋር በበይነ መረብ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤በተለያዩ ምክንያቶች የገቢዎች ሚኒስቴር ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) የተካተተበት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች መኖራቸውን ታሳቢ በማድረግ የህትመት ጥያቄ ማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እዲራዘም መወሰኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የትምህርት ስልጠና እና ደንበኞቾ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አክሊለ ታጠቅ ገልፀዋል፡፡

እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር 3 ሺህ 8 መቶ የሚሆኑ የደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፋዮች የእጅ በእጅ ደረሰኝ ያሳትማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የተናገሩት አቶ አክሊለ እስከ አሁን ከ9 መቶ የማይበልጡ ግብር ከፋዮች ብቻ በማዘዛቸው ተናግረዋል፡፡

አቶ አክሊለ አያይዘውም የተሰጠውን የጊዜ ማራዘሚያ በመጠቀም ሁሉም ግብር ከፋይ ወደ ድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ደንበኞች አገልግሎት በመቅረብ ደረሰኙን የማሳተም ሂደት እንዲጀምሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ደረሰኙን በግዜ ማሳተም አላስፈላጊ መጨናነቅን፣ እንግልትንና ከስራ መስተጓጎልን እንደሚያስቀር ዳይሬክቶሬቱ ጠቅሰው እስከ አሁን ድረስ የታተሙትን ደረሰኞች የማከፋፈል ስራዎች እንደሚጀመርም አስታውቀዋል፡፡

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ፤-ቴድሮስ ልኡልሰገድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *