በድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ለቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሰራተኞች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ

በዓለማችን ላይ ሰፊ የሥራ ዕድል ከሚፈጠሩ ኢንዱስትሪዎች መካከል ቱሪዝም ዋነኛው ሲሆን በዚህም የሆቴል እና ሬስቶራንት ኢንዱስትሪ እንዱና ዋነኛው ነው ሲሉ የባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚካኤል እንዳለ ተናግረዋል፡፡

የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ማጠቃለያ በመረሀ ግብሩ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሚካኤል ሀገራችንም የሆቴል ኢንዱስትሪን በማዘመን የቱሪሰት እርካታን በማሳደግና ቆይታቸውን በማራዘም የቱሪዝም እድገትን ለማፋጠን የመስህብ መሠረተ-ልማት፣ የማረፊያ እና መመገቢያ ሥፋራዎች (ሆቴሎች) ልማት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት በስፋት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

አቶ ሚካኤል አክለውም ያስመዘገብናቸውን ስኬቶችን ለማስቀጠል ከአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ማናጅመንት ማሰልጠኛ ተቋም ጋር በመተባበር የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ጥራትና ቅልጥፍና ለማሻሻል 250 ባለሞያዎችን በእንግዳ አቀባበልና እያያዝ፣ በምግብና መጠጥ መስተንግዶ፣ እንዲሁም በቤት አያያዝ የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማዘመን የሚያስችል ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል።

በድሬዳዋ አካባቢ በሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን የተመለከተ እውቀት በተሰማራቹበት የስራ መስክ ወደ ተግባር በመለወጥ ለዘርፉ እድገት የበኩላችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ ሲሉ የባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚካኤል እንዳለ አሳስበዋል።

በድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ለቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሰራተኞች በእንግዳ አቀባበል፣ አያያዝና መስተነግዶ/CUSTOMER CARE/ እና በቤት አያያዝ /HOUSEKEEPING/ ላይ ሲሰጥ የቆየው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እንዲሁም የእውቅና ሰርተፍኬት አሰለጣጥ ላይ የተገኙት የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ አብዲ ሙክታር ናቸው።

ኢትዮጲያ በርካታ ቅርሶች እና መስህቦችን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኒስኮ) ያስመዘገበች ቢሆንም የዘርፉ ዋና አንቀሳቃሽ የሆነውን የሆቴል እና ቱሪዝም አገልግሎት ዘርፍ የቅንጦት ሆኖ ትኩረት ሳይሰጠው እንደቆየና ልናገኝ የሚገባውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ሳናገኝ መቆየታችን ይታወቃል በማለት አቶ አብዲ ተናግረዋል፡፡

በአስተዳደራችን ከለውጥ አመራሩ ማግስት መልካም እሴቶቻችንን እና ባህሎቻችንን በጋራ ለመጠበቅ፣ ጥንታዊና የመካከለኛ ዘመን ቅርሶቻችንን በሀገር አቀፍ ቅርስነት እንዲመዘገቡ፣ የማይዳሰሱ ባህላዊ ሀብቶቻችንን በማልማት፣ ቅርሶቻችንንና መስህቦቻችንን በማስተዋወቅ መልካም ገጽታችንን ለመገንባት እንዲሁም በቱሪዝም ኢንዱስትሪ ቁልፍ ዘርፍ የሆነውን የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት ሪፎርም በማከናወን ድሬዳዋ ለምሥራቅ ኢትዮጲያ እና የአፍሪካ ቀንድ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ሰፊ ሥራዎችን እያከናወንን ነው በማለት አቶ አብዲ ተናግረዋል፡፡

በአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ላይ የተሳተፉ በአስተዳደራች ያሉ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ እንዲሁም መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ይበልጥ ጥራት እንዲኖቸው ለማስቻል እና ደረጃቸውን ከፍ ለማድረግ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት በቅርበት ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው ሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰንዝረውልናል።

ከተማዋ በቱሪዝሙ ዘርፍ እንድታድግ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለበት እንዲሁም በዘርፉ በቂ የሰለጠነ ባለሙያ እንዲኖር ለማድረግ በየጊዜዉ እንደዚህ አይነት መሰል አጫጭር ስልጠናዎችንና ድጋፎችን መስጠት አለባቸውም ብለዋል።

በዚህ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናና የእውቅና ሰርተፍኬት አሰለጣጥ የድሬዳዋ አስተዳደር የባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚካኤል እንዳለ፣ የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዲ ሙክታር፣ የሆቴልና ቱሪዝም ማናጅመንት ማሰልጠኛ ተቋም ባለሙያዎች፣ የሆቴል እና ቱሪዝም አገልግሎት ተቋማት ባለሀብቶች እንዲሁም ሰልጣኞች ተገኝተዋል።

በበድሉ ሀይሌ

ምስል፦ ተዎድሮስ ልዑልሰገድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *