በተፋሰስ ልማት ስራዎች የታዩ የህዝብ መነሳሳቶች በሌሎች የልማት ስራዎች መደገም እንደሚገባ ተገለፀ

በድሬደዋ አስተዳደር ከንቲ አቶ ከድር ጁሃር የተመራ ልዑክ በአስተዳደሩ በሚገኙ ስድስት የገጠር ቀበሌዎች የበጋ ወራት የተፈሰስ ልማት ያለበት ደረጃ ጉብኝት አድርጓል።

ጉብኘቱ የተደረገው በዋሂል ክላስተር ሃሎ ቡሳና ዱጁማ

፤በአሰሊሶ ክላስተር ገንደ ሪጌና ሁላሁሉል እንዲሁም

በቢያዋሌ ክላስተር በለዋና ቃልቻ ቀበሌዎች ነው።

በጉብኝቱ ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር እንደገለፁት የተፋሰስ ልማቱ ስራዎች በከፈተኛ የህዝብ ተሳትፎ በተያዘላቸው እቅድ መሰረት እየተፈፀሙ ይገኛሉ።

የአፈር ሃብታችን ለብልፅግናቸን በሚል መሪ ቃል ለ40 ቀናት እየተከናወነ የሚገኝው የተፋሰስ ልማት በምግብ እራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት ከማገዝ ባለፈ አየር ንብረት ለውጥን በማሻሻል ዘላቂ አረንጓዴ እኮኖሚ ለመገንባት እንደሚያስችልም ከንቲባ ከድር ጁሃር ገልፀዋል።

በሌላ በኩል የብልፅግና ፓርቲ የድሬደዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ኢብራሂም ይሱፍ መንግስት በተለይም ከለውጡ ማግስት ሰው ተኮር የሆኑ ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆናቸውን አስታውሰዋል።

የተፋሰስ ልማት ስራም ህዝቡን በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚያደርግ ከመሆኑም ባለፈ የስራ በሃልን በማሻሻል እረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀዋል።

ስራው በከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ እየተከናወነ እንደሚገኝ በጉብኝቱ መታየቱን በጥቅሉ በተፋሰስ ልማት ስራዎች የታዩ የህዝብ መነሳሳቶች በሌሎች የልማት ስራዎች መደገም እንደሚገባ እንደሚገባ አቶ ኢብራሂም ገልፀዋል።

የድሬደዋ አስተዳደር ግብርና ውሃ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም በተከናወኑ የተፋሰስ ልማት ስራዎች በተሰሩ ስራዎች የአየር ንብረትና የገጠሩ አካባቢ ገፅታ ከመሻሻሉ ባለፈ በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነት መጨመር አስተዋፆ ማድረጉን ገልፀዋል።

የበጋ ወራት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎቹ በዘርፍ ተከፍለው እየተከናወኑ በሆናቸውን የገለፁት አቶ ኑረዲን በጋራ ላይ አፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች የድንጋይ ክትር ፣ የጋራ እርከን ፣ የድንጋይና የአፈር እርከን ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

በማሳ ውስጥ የሚከናወኑ ስራዎች የማሳ እርከን ጥገና ፣ ፍግ ወደ ማሳ ማጋዝ ፣ የቀራ ነቀላ ስራዎች እንዲሁም ከመስኖ ሰወራ ጋር በተያያዘ ምንጭ ማጎልበት ፣ ኩሬና የውሃ ካናል ደለል ጠረጋ ተግባራት በእቅዳቸው መሰረት እየተፈፀሙ መሆኑን በአጠቃላይ በተፋሰስ ልማት ስራው 5500 ሄክታር መሬት ለመሸፈን ታቅዶ እስካሁን 56 በመቶ ማለትም 3080 ሄክታር መፈፀም መቻሉን አቶ ኑረዲን አብራርተዋል።

በተፋሰስ ልማት ስራው ከአፈርና ውሃ ጥበቃ በተጨማሪ ከጤና፣ትምህርት እንዲሁም ከበጎ አድራጎት ስራዎችን ነዋሪውን በማሳተፍ እየተከናመኑ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

በዳግማዊ ፍቃዱ

ፎቶ ፦አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *