ጠንካራ የፓርቲ ግንባታ እውን በማድረግ ለትውልድ የሚሻገር ዘላቂ ተቋማት ግንባታ ላይ ተጨባጭ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ሱሉ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ ኢብራሂም ዩሱፍ ገለጹ

ብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው ከአንደኛው እስከ ሁለተኛው መደበኛ ጉባኤው ያሉትን ስራዎች የገመገመ ሲሆን ያሳለፋቸው ትልልቅ ውሳኔዎች መኖራቸውን ገልጸው ከእነዚህ ውሰጥም የጠንካራ ፓርቲ እና የጠንካራ መንግስትን በተመለስተ ትኩረት በሚሹ ዕቅዶቹ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የጠንካራ ፓርቲ መኖር የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት እንዲሁም የተሳለጠ የሕዝብ አስተዳደር ሥርዓት ለመፍጠር ቁልፍ ድርሻ አለው ብለዋል ።

ለዚህም የፖሊሲ ወጥነት በመፍጠር በፌደራልና በክልሎች መካከል ቅንጅትን በማጠናከር ረገድ የጠንካራ ፓርቲ እውን መሆን ጉልህ ሚና እንዳለውም ነው ያነሱት።

ቀጣይ በትኩረት ከሚሰራባቸው ጉዳዮች መካከል ጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ለጠንካራ መንግሥት እውን መሆን ከቁልፍ አጀንዳዎች መካከል አንዱ ነው ብለዋል ::

አቶ ኢብራሂም አክለውም ጠንካራ ፓርቲ እንዲሁም ተቋማት ግንባታ ላይ ሰፋፊ ሥራዎች በመሰራታቸው ተጨባጭ ውጤቶች መጥተዋል ነው ያሉት።

የፓርቲውን የፖለቲካ አደረጃጀት ማጠናከር ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ዘላቂነት ባለው መንገድ ሀሳቦችን ወደ መሬት በማውረድ የሕዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ፓርቲ ግንባታ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ዴሞክራሲያዊነትን የሚያረጋግጡ፣ ሁሉም የአደረጃጀትና የፖለቲካ ሥራዎች በተሻለ ጥራትና ብቃት መከናወናቸውን የገለጹት ሀላፊው በተለይም በዲፕሎማሲው ረገድ የተመዘገቡ አበረታች ድሎች መኖራቸውን ኣብራርተዋል።

በቀጣይ ዓመታትም ለዘመኑ የተቀረጹ ተልዕኮዎችን እና የተጀመሩ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ስራዎች በስኬት እንዲቀጥሉ የፓርቲውን አመራር የማጥራት፣ የማጠናከርና የመገንባት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል፡፡ ብልፅግና ፓርቲ በሰጠው ጠንካራ አመራር ቅቡልነት ያለው የሀገረ መንግስት ግንባታን የሚያፋጥኑ ስራዎችን ማከናወን መቻሉንም ጠቁመዋል።

Diretv

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *