አዲስ አበባ እያስመዘገበች ያለው ፈጣን ዕድገት የሚደነቅ ነው

አዲስ አበባ እያስመዘገበች ያለው ፈጣን ዕድገት የሚደነቅ መሆኑን የሀገራት መሪዎች መናገራቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ትናንት የተጀመረው 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ይገኛል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ዛሬ የተካሄዱ ሁነቶችን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ዛሬ በነበሩ የተናጠልና የጋራ ውይይቶች ላይ የተሳተፉ የሀገራት መሪዎች ፤ አዲስ አበባ እያስመዘገበች ያለው ፈጣን ዕድገት የሚደነቅ ስለመሆኑ መናገራቸውን አንስተዋል፡፡

መሪዎቹ በአንድ ዓመት ውስጥ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች ተከናውነው ማየታቸውንም ስለመግለጻቸው ጠቁመዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው በዛሬው ዕለት የኅብረቱ ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ማካሄዱን ጠቁመው ፤ የአፍሪካ የደህንነትና ፀጥታ ምክር ቤት ውይይት አንዱ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ የሚለው እሳቤ ከቃል ባለፈ በተግባር ለማመላከት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አፅንኦት ተሰጥቷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *