በውይይት መድረኩ ፓርቲው በ2ተኛ መደበኛ ጉባኤው ያስተላለፋቸው ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ማጠናከር ፣ ማህበራዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ ፣ የብሄራዊነት ገዢ ትርክት ግንባታን ማጠናከር ፣ ውጤታማ የሰላም ግንባታ፣ የሃገር ግንባታ፣ የፍትህ ዘርፍ ውጤታማነትን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ልማትን ማፋጠን፣ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራዎችን መስራት፣ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርምን ውጤታማነት ማረጋገጥ፣ ጠንካራ የኮሚኒኬሽን ስራዎችን መስራት በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ለተሳታፊዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
እስከ ቀጣይ ጉባኤ እነዚህ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ከሚጠበቀው በላይ ለማሳካት እና ውጤታማ ስራዎች እንዲሰሩ ለማስቻል የፓርቲው አባለት፣ ደጋፊ አባላት እና ህብረተሰቡ በጋራ ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ተብሏል፡፡
የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ለስኬት እንዲበቁ በተለይ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የመፍታት፣ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች በእኩል ተደራሽ ማድረግ እና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አኳያ አመራሩ እና ህብረተሰቡ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ከመድረኩ ተሳታፊዎች ተነስቷል፡፡
አክለውም የተገኙ ውጤቶችንም አጠናክሮ ለማስቀጠል ህብረተሰቡ ከአመራሩ ጎን በመቆም የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ድጋፍ እናደርጋለን ሲሉ ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል፡፡


