የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፍሪካዊ መፍትሄ የታየበት እና ትምህርት የሚቀሰምበት መሆኑ ተገለፀ

በፌዴራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል ጥቅምት 23/2015 የተካሄደው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በተግባር የተፈፀመበትና ትምህርት የሚቀሰምበት መሆኑ ተገልጿል።

የስምምነቱን ሂደት በተመለከተና ከስምምነቱ ሌሎች ምን እንማር? በሚል በአፍሪካ ህብረት ሪፓርት ቀርቧል ።

ስምምነቱ በአፍሪካውያን እንዲፈፀም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከመጀመሪያው ቀን ጀምረው በቁርጠኝነት መስራታቸውም ተገልጿል ።

የሰላም ስምምነቱ ከወረቀት ባለፈ በተግባር የታየበት መሆኑም ነው የተገለፀው።

የአፈፃፀም ሪፓርቱን ተሰናባቹ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፉኪ ማህማት፣ የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪ ቡድን አባል ኡሊሲንጎን ኦባሳንጆ እና ከፍተኛ ኮሚሽነሮች አቅርበዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የፌዴራል መንግሥትን በመወከል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እና ሌሎች የፌዴራል መንግሥት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ እና የህወሓት አመራሮች ተገኝተዋል።

EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *