በአስተዳደሩ በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ነዎሪዎች ከቃል እሰከ ባህል በሚል መሪቃል የሚያካሂዱት ውይይት በወረዳ 01 እና በወረዳ 02 የግንዛቤ መድረክ ውይይት ተደርጓል።
በወረዳ 01 በተካሔደው ህዝባዊ ውይይት የተገባውን ቃል ለመፈጸም እና ነዋሪውን በታማኝነት ለማገልገል ውጤታማ ስራ ለመስራት በአስር ይዘቶች ተከፍለው የተዘጋጁትን የመወያያ ሰነዶች ከቃል እስከ ባህል ፣ ብሔራዊ ትርክትን ማፅናት፣ ውጤታማ የሠላም ግንባታ ለመሰራት የህዝብ ተግባቦት ወሳኝ እንደሆነ የገለጹት የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ሀላፊ እና የወረዳው ደጋፊ አመራር አቶ አብዲ ሙክታር ናቸው።
በተመሳሳይም የወረዳ 02 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አቤል ምስራቅ የውይይቱን አላማ አስመልክተው ባደረጉት ገለጻ እንዳሉት የብልጽግና ፓርቲ በ2ኛ ጉባኤው ከቀደመው ጉባኤ እስካሁኑ ድረስ ያሳካቸውን ዋና ዋና የልማትና የመልካም አስተዳደር ሀገራዊ ድሎች ይበልጥ ለማስቀጠል በ2ኛው ጉባኤ ያስቀመጣቸውን አበይት ውጤቶችና አቅጣጫዎችን ለማውረድ በማለም መሆኑን ገልጸዋል።
ፈጣን ኢኮኖሚን ማረጋገጥ ፣ ማህበራዊ የብልጽግና ስራዎችን ማስጠበቅና ውጤታማ ስራዎች ን ማሰቀጠል የተጀመረውን የለውጥ(ሪፎርም) ውጤቶች ማረጋገጥ በተመለከተ አንኳር ነጥቦች ላይ ነዋሪዎቹ ተወያይተዋል።
Dire tv


