የብልጽግና ፓርቲ ከቃል እስከ ባህል ብሄራዊ ትርክት ዙሪያ የዋሂል ክላስተር ኮሪሶ ወረዳ የፓርቲው አባላት ውይይት አካሄዱ።

በዉይይቱ ህብረ ብሄራዊ መግባባትን በሃሳብ አንድነት ለማጠናከር ብሄራዊ ትርክቶችን ለሁሉም ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ እና የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የተቀመጡ የፓርቲው አቅጣጫዎች ላይ ገንቢ ሃሳቦች ተንሸራሽረዋል።

በግብርናው ዘርፍ እንደ ሀገር የተመዘገበው ወቅትን ያላማከለ ውጤታማነት በጥሩ አፈጻጸም በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ መነሳቱ የተገለጸ ሲሆን በድሬደዋም ለግብርና ምቹ ባልሆነ አየር ንብረት ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉ በተለያየ ጊዜ መነሳቱም የዋሂል ክላስተር ኮሪሶ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ባደረጉት ውይይት ተነስቷል።

የብልጽግና ፓርቲ የግብርናው ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል አርሶ አርብቶ አደሩ መደገፍ እንዳለበት በትኩረት አቅጣጫነት የተቀመጠ በመሆኑ መንግስት ለአርሶ አርብቶ አደሩ የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በውይይቱ ተገልጿል።

የዋሂል ክላስተር ኮሪሶ ወረዳ ፓርቲ አባላቶች የፓርቲው አቅጣጫ ዙሪያ የተቀመጡ ሃሳቦች ላይ በየጊዜው የሚደረጉ ምክክሮች ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑን ጠቅሰው እየተደረገላቸው ያለው ድጋፍና ክትትል በጥሩ ጎኑ የሚወሰድ ሆኖ ሳለ የገበያ ትስስር በመፍጠሩ በኩል ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አስገንዝበዋል።

DIRE TV

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *