የከተማ ስራ አስኪሃጅ ፅ/ቤት እና ተጠሪ ተቋማት የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አባል የደንብና መመሪያ ዙሪያ የግናዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ የመወያያ ፅሁፍ ያቀረቡት የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የሴቶች ክንፍ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አይናለም መንገሻ ሴቶች የማህበራዊና ኢኮናኖሚያዊ ብልፅግና ግንባታ ሂደት ድርሻ እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በአስተዳደሩ በሁሉም ወረዳዎች የሴቶች ክንፍ አደረጃጀት ተዘርግቶ የሴቶችን ተሳትፎ ለማጎልበት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ይህን አደረጃጀት በመንግስት ሰራተኞች ዘንድ ለማስፋት የግናዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት እየተሰሩ መሆናቸውን ወ/ሮ አይናለም አስረድተዋል።
በየደረጃው በሚገኙ የመንግስት አስተዳደር እርከኖች ሴቶች እራሳቸውን በማጎልበት ለሃላፊነት እንዲበቁ የሚያደርጉ ተከታታይነት ያለው መሰል የአቅም ግንባታ ስራዎች እንደሚከናወኑ የጠቆሙት ወ/ሮ አይናለም የዛሬውን መድረክ ላዘጋጀው የከተማ ስራ አስኪሃጅ ፅ/ቤት መስጋናን አቅርበዋል።
ሌሎች ተቋማትም የሴቶችን አቅም የሚያጎለብቱ ተግባራትን ከመደበኛው የስራ ተልዕኮ ጎን ለጎን ማከናወን እንደሚገባቸው ገልፀዋል።
በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ደንብና መመሪያ በሰፊው ተብራርቶ የቀረበ ሲሆን በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
ዳግማዊ ፍቃዱ
ፎቶ፦ሰላም አበበ


