በሥራና ክሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ የተመራ የልኡካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 08 እና ዐ4 የተሰሩ የከተማ ምግብ ዋስትና ሥራዎችን ገምግመዋል።
ሚኒስቴር ድኤታው በፖለቲካ ሉኣላዊነት የተቀናጀነውን ድል በኢኮኖሚውም መድገም አለብን ሲሉ ገልፀዋል። ኢትዮጵያ ቀና ብላ እንድትሄድ ለማስቻል በሁሉም ዘርፍ ፍሬያማ ሥራ መሰራት አለበት ብለዋል። በተለይ በሴፍቲኔት ተረጂ የሆኑትን ግለሰቦች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ማስገባት አለብን ብለዋል።
በዚህም በ08 እና በ04 ግምገማ ያካሄዱ ሲሆን በ08 በዶሮ እርባታ ፣ በእንጨት ስራ ፣ በንግድ ከደሃ ደሃ ተረጂነት የወጡ ነዋሪዎችን ህይወት በተግባር ተዘዋውረው ተመልክተዋል ::
በ04 ወረዳ ሪፖርትን ያደመጡ ሲሆን በወረዳው በሴፍቲኔት ኘሮግራም ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን የወረዳ 04 ስራ አስፈላሚ አቶ እስማኤል አብዱለጢፍ አብራርተዋል። በወረዳው ትክክለኛ የደሃ ደሃ የሆኑትን ክፍሎች በመለየትና በመሰብሰብ ሂደት በወረዳው 311 ኑሯቸውን ጎዳና ያደረጉ ፣ 122 ለምኖ አዳሪ 274 ሴተኛ አዳሪዎችን በመለየት 177 የሆኑትን ህይወታቸው መቀየር እንደተቻለ ጠቁመዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው በወረዳው እየተሰራ ያለውን ሥራ አድንቀው ድህነትን በማጥፋት የአፍሪካዊ ሃያል የሆነች አገር መገንባታችንን በተጨባጭ እውን እናደርጋለን ብለዋል።
dire tv


