#DGC የካቲት 17/2017
የኮሪደር ልማት ስራዎች በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ አካባቢዎች በስፋት እየተሰራ ሲሆን በዛሬው እለትም በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር የተመራ የካቢኔ አባላት ቡድን እየተገባደደ የሚገኘውን የ 11 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራዎች ተዟዙረው ተመልክተዋል ።
በጉብኝቱ ወቅትም ከኮሪደር ልማት ስራ ተቋራጮች ጋር የተወያዩት ክቡር አቶ ከድር ጁሃር ፕሮጀክቱ በጥራትና በፍጥነት እንዲጠናቀቅም አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።
በተለይም የሥራ ባህልን እየለወጠ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ሥራው ድሬዳዋን ፅዱና ምቹ እንደሚያደርግ ጠቅሰው ልማቱ ተቀናጅቶ የመስራትን ልምድ በሌሎች ፕሮጀክቶች ለመድገም ተሞክሮ የሚቀሰምበት እንደሆነም በእለቱ ገልጸዋል ።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በበኩላቸው የኮሪደር ልማትና ሌሎች ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ለህብረተሰቡ ለማስረከብ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል ፡፡
የካቢኔ አባላቱን የኮሪደር ልማት ሥራው በተቀናጀ መንገድ ዳር ለማድረስ ድጋፍና ክትትላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል ፡፡
በአለማየሁ አበበ
ፎቶ :- በአገኘው ሸዋረጋ


