ኘሮጀክቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚቋቋመው የአርበቶና የከፊል አረብቶ አደር የመስክ ትምህርት ቤቶች በአመቻችነት ለሚያገለገሉ አስተባባሪዋች ሰልጠና
ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በተለያዩ ክልሉች የአርበቶና የከፊል አረብቶ አደር የመስክ ትምህርት ቤቶች ያስመዘገበው ለውጦች በመታየቱ በድሬዳዋ አስተዳደር ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚቁቀሙ የአርበቶና የከፊል አረብቶ አደር የመሰክ ትምህርት ቤቶች አስተባባሪዋች በ4 ወረዳዋች ለሚገኙ ስልጠናው መዘጋጀቱን የገለፁት በድሬዳዋ አሰተዳደር ውሃ መአድንና ኢነርጂ ቢሮ የቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ አቶ ኢሳም ሁሴን ናቸው።
ኘሮጀክቱ ተነድፎ የመጀመሪያው ምእራፍ ተግባራዊ በተደረገባቸው ክልሎች አርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር የኑሮ ሁኔታ በዘላቂነት ለማሻሻል ዘርፈ-ብዙ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው በርካታ ጅምር ስኬቶች መመዝገብ መቻላቸውንም አቶ ኢሳም ጨምረው ገልፀዋል።
የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀከት በድሬደዋ አሰትዳደር ገጠር አርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር ወረዳዎች በፕሮጀክቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚቁቀሙ የአርበቶና የከፊል አረብቶ አደር የመሰክ ትምህርት ቤቶች በአመቻችነት ለሚያገለገሉ ተሳታፊዎች ስልጠናው መሰጠቱ በማቋቋም እና በማደራጀቱ የድርሻቸውን እንዲወጡ ያስችላቸዋል ሲሉም አቶ ኢሳም ገልፀዋል ፡፡
የአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር የመሰክ ትምህርት ቤቶቸ በሀገራቸን በተለያዩ ክልሎች መተግበር ከተጀመረ አመታት ያሰቆጠረ ቢሆንም በድሬዳዋ ፕሮጀከቱ ባመጣው መልካም አጋጣሚ ለመጀመሪያ ጊዜ የአመቻቾቸ ሰልጠና መስጠት በመቻሉ ሰልጣኞቸ በቀጣይ ለሚቁቃሙ ሰምንት ትምህር ቤቶቸ አርበቶ አደሩና ከፊል አርብቶ አደሩ በተግባር በመሰክ ላይ በመረጡት ትኩረት የግብርና ስራ በተግባር የሚሰለጥኑ ይሆናል ፡፡


