በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በደኦ የተመራ ልኡካን ቡድን ድሬዳዋ ገባ

ልዑክ ቡድኑ ድሬዳዋ የገባው በነገው እለት የሚከበረው ማርች 8 ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ሲሆን፤ ዛሬ ከሰአትም የተለያዩ የልማት ስራዎችን ልኡክ ቡድኑ የሚጎበኝ ይሆናል።

እንግዶቹ የድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋአረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *