በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የኮሪደር ልማት ስራዎች በስፋት እየተሰሩ ሲሆን እነዚህም የኮሪደር ልማት ስራዎች ጥራታቸውን ጠብቀው ይሰሩ ዘንድም የክትትል እና ቁጥጥር ስራዎች ተጠናክሮ እየተከናወነ ይገኛል ።
በዛሬው እለትም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህን ጨምሮ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ከሰብሪያ ሆቴል አንስቶ እስከ ፋይናንስ እየተሰራ ያለውን የኮሪደር ልማት ኘሮጀክት ጎብኝተዋል ።
ፎቶ :- በአገኘው ሸዋረጋ


