/አደንዛዥ እጽን እና ሱሰኝነትን መከላከል የሁሉም ማህበረሰብ ኃላፊነት መሆኑ ተገለፀ::

የድሬ ፍሬዎች በጎ አድራጎት ማህበር ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለህዳሴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች አደንዛዥ እጽን እና ሱሰኝነትን መከላከል ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር የወረዳ 06 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አባስ አሊ በሱስ ምክንያት የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቀነስ እንደነዚህ አይነት ግንዛቤን የሚያዳብሩ ስልጠናዎች ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳላቸው ገልፀዋል።

አቶ አባስ አያይዘውም አደንዛዥ እጽን እና ሱሰኝነትን መከላከል የሁሉም ማህበረሰብ ኃላፊነት መሆኑ ገልፀው፤ ሰልጣኝ ተማሪዎች ስልጠናውን በነቂስ በመከታተል ተግባራዊ ማድረግእንደሚገባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የድሬ ፍሬዎች በጎ አድራጎት ማህበር መስራችና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ወሰን ቢራቱ በበኩላቸው ሱስና አደንዛዥ እፅ በአሁኑ ወቅት ትውልዱን በከፍተኛ ደረጃ እየጎዳ እንደሆነ ጠቁመው፤ሱሰኝነት በሰዎች ላይ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት እንደሚያስከትልም አብራርተዋል።

የዛሬው የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ዋነኛ አላማም ተማሪዎች ስለሱስ አስከፊነት እንዲያውቁ ማስገንዘብ መሆኑን አቶ ወሰን ጠቁመው ይህ የግንዛቤ መፍጠሪያ ስልጠና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:- ሰላም አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *