የውይይት መድረኩንም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ አስጀምረውታል።
በአሁኑ ሰአትም በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት ምክትል እንዲሁም በፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻኪር አህመድ “የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” በሚል ሰነድ እየቀረብ ይገኛል።
ከለውጥ መንግስት ምስረታ ጀምሮ ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት በሀገራችን ኢትዮጵያ ከተገኙ አበይት ለውጦች መካከል ሀገራዊ የፖለቲካ ለውጥ፣ ሀገራችንን ወደ ላቀ ምዕራፍ በማሸጋገር ላይ ያለው የኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ፣ ተቋማዊ ሪፎርም ስኬቶችና ሀገራዊ ዲፕሎማሲያዊ ድሎች በዋናነት ይጠቀሳሉ።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋረጋ


