#DGC መጋቢት 26/2017
በድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ፣ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ በተኪ ምርት ስትራቴጂ ፕላን እና በአምራች ኢንዱስትሪና አቅም ልማት ዙሪያ ለቢሮው ማኔጅመንት አባላት እና ለድሬ ታምርት ንቅናቄ ክላስተር ኮሚቴ የአቅም ልማት መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ የቢሮው ምክትል እና አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ አብዲ ሙክታር አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሰለጠነ የሰው ሃይል በበቂ ደረጃ እንዲኖረ ማድረግ እንደሚገባ የገለፁ ሲሆን አሁን ላይ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ በአዲስ ፀድቆ ስትራቴ ጂ ወጥቶለት እየተከናወነ ይገኛል ይህንን አውቆ መንቀሳቀስ በዘርፉ ካሉ ባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ብለዋል።
የአምራች ኢንዱስትሪው ቋሚ የስራ እድል ለመፍጠር ትልቅ አስተዋፅኦ ስለሚያደርግ መንግስት ለዘርፉ እጅግ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የፋይናንስ አቅርቦትና የኢንቨስትመንት ማበረታቻ እያደረገ እንደሚገኝ አቶ አብዲ ገልፀዋል።
በቀጣይም ለዘርፉ የተሰጡ ትኩረቶችን በመገንዘብ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሃብቶችም ሆኑ ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት በቅንጅት በመስራት የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ መስራት እንደሚገባ ምክትለ ቢሮ ሃላፊው ጠቁመዋል።
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የስትራቴጂ ጉዳይ ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን አባይ እንደ አገር አምራች ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ የተለያዩ ስትራቲጂዎች እየተተገበሩ እንደሚገኙ ገልፀው ከዚህ ውስጥ ተኪ ምርት ማስፋፋት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
እንደ ሀገር መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት ማለትም ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ብዝሃመር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር እየተሰራ አንደሚገኝ አቶ ጥላሁን ተናግረዋል።
ቀደም ባሉት ጊዜያት የነበሩ የአምራች ኢንዱስትሪ ስትራቴጂዎች ኤክስፖርት ላይ ያተኮረ እንደነበር፣ ይሁን እንጂ የሌሎች አገራትም ተሞክሮ የሚያሳየው በተኪ ምርት ላይ በማተኮርና አቅም በመገንባት ወደ ኤክስፖርት መሸጋገር በመሆኑ አሁን የተቀረፀው ፖሊሲ በዚህ ላይ ያተኮረ እንደሆነ አቶ ጥላሁን ጠቁመዋል።
አዲስ የፀደቀው ፖሊሲ ገበያ መር ፣ የተገደበ የመንግስት ጣልቃ ገብነት፣ የተመጣጠነ የወጪና ገቢ ንግድ በግሉ ዘርፍ የሚመራ የኢንዱስትሪ ክላስተር ማስፋፋት መርሆዎች በመያዝ የማይክሮ ኢኮኖሚና ቢዝነስ ምህዳር ማስፋት፣ ፋይናንስ የሰው ሃይል ልማትና አስተዳደርን ማጎልበት፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ማጠናከር ምርት ልማትና ተወዳደሪነትን ማላቅ አቅጣጫዎች ተከትሎ እንደሚተገበር ገልፀዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ እንደሀገር ለኢኮኖሚው እያበረከተ ያለውን አስተዋዕዖ ለማላቅ የሰው ኃይል ልማት ላይ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች እንዲሁም የሚለከታቸው አካላት በቅንጅት በመሆን የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለማረጋገጥ የድርሻቸውን መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል።
መረጃ:-ን/ኢ/ኢ/ቢሮ ህዝብ ግንኙነት


