#DGC መጋቢት 26/2017
በተጨማሪም በዚህ አመት ለ 457 ነጋዴዎች በመንግስት የመስሪያ ቦታ ምችችት የተደረገ ሲሆን ከ 1 ሺ ካሬ ሜትር በላይ ተጨማሪ መሬት መዘጋጀቱንም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ለነጋዴዎች አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ ህንፃ እንዲገነባ የመሬት ድጋፍ እየተደረገ ሲሆን ነጋዴዎችም የተሻለ ህንፃ እንዲሰሩ ካርታ መሰጠቱ ተገልጿል።
በአንድ ወር ጊዜ ውስጥም እየተሰበሰበ ያለውን ሀብት ለአደጋው ተጎጂዎች እንደየ ድርሻቸው እንደሚከፋፈለም የተገለፀ ሲሆን እስከዛሬም የዘገየው በሀገራችን በጎፋ አካባቢ በተከሰተ የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የሰው ህይወት በመጥፋቱ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ሲደረግ በመቆየቱ እንዲሁም በተለያየ ጊዜ ቃል የገቡ ወገኖች ገቢ ባለማድረጋቸው መሆኑ ተጠቁሟል።
ማንኛውም አይነት የተነሱ ቅሬታዎችም በአጭር ጊዜ መፍትሄ እንዲያገኝ ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በመስተዳደሩ በተከፈቱት አካውንቶች ማለትም
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000637750201፣ የዳሽን ባንክ 5009786342011 እንዲሁም የአዋሽ ባንክ 013211367855100 እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1001300318808 የሂሳብ ቁጥር በተጨማሪም በአቢሲንያና በራሚስ ባንክ ብሎም በተለያየ መልኩና በአይነትም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል፡፡


