#DGC መጋቢት 27/2017
በኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር የምስራቅ ግንባር ደረጃ 3 ሆስፒታል የ9 ዙር የክሊኒካል ነርስ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ውድድር ተጀመረ
ስፖርታዊ ፌስቲቫሉ በዋናነት ሰራዊቱ በአካል፣ በመንፈስ፣ በስነልቦና እና በማህበራዊ ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ወንድማማችነት ለማጠናከር እንደሆነ ተገልጿል።
በመርሀግብሩም ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የምስራቅ ግንባር ሆስፒታል አዛዥ ኮ/ል ብርሃኑ ዘውዴ ስፖርታዊ ፌስቲቫሉ መዘጋጀቱ ጥቅሙ የጎላ መሆኑን አንስተው የምስራቅ ግንባር ደረጃ 3 ሆስፒታል ዘመን ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅሞ ህክምናውን ሰራዊቱ በተሰማራበት ሀገራዊ ግዳጅ ቆስለው የመጡ አባላትን በፍጥነት አክሞ ለግዳጅ ዝግጁ በማድረግ በከፍተኛ ሀይል የአጋዥነት ሚናውን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
ሆስፒታሉ ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን በባለፉት በርካታ አመታት በተለያዩ የሙያ መስኮች ከተለያዩ እዞች የተቀበላቸውን ከ800 በላይ የክሊኒካል ነርስ ተማሪዎች ማስመረቁን ገልጸዋል።
በመርሀ ግብሩም የምስራቅ ግንባር ደረጃ 3 ሆስፒታል የ9 ዙር የክሊኒካል ነርስ ተማሪዎች የተለያዩ ስፖርታዊ ትርዒቶችን ና ውድድሮችን አቅርበዋል።
የምስራቅ ግንባር ደረጃ 3 ሆስፒታል በቅርቡ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በመርሀ ግብሩም ብ/ጄነራል ማርዬ ምትኩ የምስራቅ እዝ የሰራዊት ስነልቦና ግንባታ ሀላፊ፣ የምስራቅ አየር ምድብ የአየር ሀይል አመራሮችና አባላት እና በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ሰላም ለማ
ምስል:- አገኘው ሸዋረጋ


