የቬይትናም ልምድ ለኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ምሳሌ የሚሆን ነው፦ ቢልለኔ ስዩም

ቬይትናም በብዙ ዘርፍ ያመጣችው ተጨባጭ ለውጥ ለኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ምሳሌ ሊሆን እንደሚችል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ተናግረዋል።

በሃምሳ ዓመታት የኢትዮ-ቬይትናም የዲፕሎማሲ ግንኙነት ታሪክ በመሪ ደረጃ የተደረገው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጉብኝት በመንግሥት እና በፓርቲ አመራሮች ደረጃ ጠቃሚ ውይይቶች መደረጋቸውን አስታውሰዋል፡፡

ቬይትናም የሶላር ፓነሎችን እያመረተ ወደ ውጭ የሚልክ ቶዮ ሶላር ፋብሪካ እንዳላት የጠቀሱት ቢልለኔ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የመሩት ልዑክ በፋብሪካው ጉብኝ ማድረጉን እና ፋብሪካው ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ዞን ሥራ እየጀመረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሃኖይ ስማርት ሲቲ በልዑካን ቡድኑ የተጎበኘ ሌላው ቦታ መሆኑን ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያ ለጀመረችው ከተሞችን የማሻሻል ሂደት ትልቅ ትምህርት የተገኘበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተገኙበት ዋናው ዓላማ አጋርነት ለዕድገት (P4G) ጉባዔ መሆኑን ያወሱት ኃላፊዋ፣ ይህም የአየር ንብረት ለውጥን ያማከሉ ልማቶች የሚመጡበት ላይ የሚሠራ እና ኢትዮጵያ አባል መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *