ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካዛንቺስን የኮሪደር ልማት በይፋ መረቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካዛንቺስን የኮሪደር ልማት በይፋ መረቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምረቃው ወቅት፥ ከተሞቻችንን የማዘመን ሰፊ ጥረት አይነተኛ ማሳያ የሆነውን በካዛንቺስ ያለዉን የኮሪደር ልማት ክፍል በይፋ መርቀናል ብለዋል።

የተጎሳቆሉ እና በእጅጉ የተጎዱ ቤቶች እና ከባቢ መገኛ የነበረው ካዛንቺስ ዛሬ የጋራ ጥረት እና ለውጥ ሽልማታችን ሆኖ ተገኝቷልም ነው ያሉት።

ከዚሁ አካባቢ ተነስተው ለማኅበረሰባችን የከበረ የኑሮ ሁኔታን ለመፍጠር ያለንን ፅኑ እምነት እና ተግባር በሚያሳይ አኳኋን ለኑሮ ወደ ተሻለ ከባቢ የተዛወሩትን ነዋሪዎች ከጥቂት ቀናት በፊት ጎብኝተን ነበር ሲሉም አስታውሰዋል።

የተዛወሩበት ከባቢ እጅግ ምቹ መሆኑን አይተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዛሬ ደግሞ የተነሱበትን ሰፈር ድንቅ የኮሪደር ልማት ሥራ መርቀናል ብለዋል።

በአስደናቂ አጭር ጊዜ የተጠናቀቀው የካዛንቺስ ለውጥ ለዘመነ ከተማ ልማት ሥራችን ለአረንጓዴ፣ ንፁህ እና ዘመናዊ የከተማ ማዕከላት ያለንን ርዕይ ግዘፍ ነስቶ በማሳየት መሠረት የሚጥል ነው፤ በዚህ ግዝፈት የሚከወኑ ሥራዎች ሰፋ ያለ ጥረት ይሻሉም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ጊዜያዊ ምቾት የሚነሱ ፈተናዎችንም ሊያስከትሉ ይችላሉ፤ ነገር ግን ለታላቁ የሀገር ጥቅም የሚከፈሉ አስፈላጊ መስዋዕትነቶች ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይኽ የእድገት መንገድ መቀጠል ያለበት መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም የታደሰ ተስፋ ይሰጣል፤ በተለይ ለልጆቻችን ነገ ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *