የኢትዮጵያ ትንሳኤ ቅርብ ነው፤ እኛም እናያለን፣ ልጆቻችንም ይወርሳሉ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትንሳኤ በዓልን በገላን ጉራ ከሚገኙ የካሳንቺስ የልማት ተነሺዎች ጋር አሳልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት፥ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ቅርብ ነው፤ እኛም እናያለን፣ ልጆቻችንም ይወርሳሉ ብለዋል።

ጎስቋላ የነበረውን ከተማ እንቀይረው ያልነው ለጋራ ጥቅም፣ ለልጆቻችን ደስታ እና መጻኢውን ዘመን ለማሳመር ብቻ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የተለወጠችና ከልመና የወጣች ሀገር እውን ከማድረግ ውጪ ሌላ ሀሳብ የለንም ሲሉ ገልፀዋል።

ለልማት ተነሺዎቹም “ቀድሞ የኖራችሁበትን ሰፈራችሁን ሄዳችሁ እንድታዩት እጋብዛለሁ” ብለዋል።

ቃል በገባነው መሰረት ካሳንቺስ እጅግ ውብ ሆኗል፤ ልጆቻችን ተስፋ አላቸው፣ ከእኛ የተሻለ ሕይወት መኖር ይችላሉ ሲሉ አመላክተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *