ከብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሚያዝያ 17 እስከ18/ 2017 ዓም መደበኛ ስብሰባውን በአዲስ አበባ አካሂዷል። በዚህ ስብሰባም የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች በዝርዝር ተመልክቷል።

ኢትዮጵያ በ2018 ከተስፋ ወደሚጨበጥ ብርሃን ለመሻገር፤ በ2023 የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ለመሆን፤ በ2040 ደግሞ ዓለም አቀፍ የብልፅግና አርአያ ለመሆን ያስቀመጠችው ርእይ እንደሚሳካ የሚያረጋግጡ የስኬት ፍንጮች መታየታቸውን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አረጋግጧል። እነዚህ የስኬት ፍንጮች የያዝነው ፍኖተ ብልፅግና ትክክል መሆኑን አመላክተውናል።

ከብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በኋላ አያሌ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች ተመዝግበዋል። ከተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በየደረጃው የሚደረገው ምክክርና ትብብር በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ወደ አዲስ ምእራፍ ገብቷል። ከአንድ ክልል በስተቀር፣ ለሀገራዊ ምክክር አጀንዳ የማሰባሰብ ምእራፍ በሁሉምክልሎች ተጠናቅቋል።

በሀገሪቱ የጸጥታ ችግር በነበረባቸው አንዳንድ አካባቢዎችም ሰላም እየሰፈነ ነው። መንግሥት በተደጋጋሚ ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ እጅ የሚሰጡ እና ወደ ሰላም ድርድር የሚመጡ ታጣቂዎች ከዕለት ወደ ዕለት ቁጥራቸው እየጨመረ ይገኛል። የመንግሥት ሕግ የማስከበር እና የማድረግ ዐቅም እየጎለበተ መጥቷል።

ከሶማሊያ ጋር ተፈጥሮ የነበረው ውዝግብ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ተፈትቷል። ኢትዮጵያ የባሕር በር እንዲኖራት የተያዘው አቋም ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነቱ እየጨመረ ነው። ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ያላት ግንኙነት ከመሻሻሉም በላይ የሚደረግላት ድጋፍ እያደገ ነው። በዓለም አቀፍ መድረክ የኢትዮጵያ ተፈላጊነት ጨምሯል። የዲፕሎማሲ ግንኙነቷም በሁሉም አቅጣጫ ከፍ ብሏል።

እስከአሁን ያለው አፈፃፀም የሚያሳየው በያዝነው ዓመት አጠቃላይ ኢኮኖሚው በታቀደው መሠረት በ8.4 በመቶ የሚያድግ መሆኑን የሥራ አስፈጻሚው ገምግሟል። በዘርፍ ደረጃ ደግሞ ግብርና በ6.1 በመቶ፣ ኢንዱስትሪ በ12.8 በመቶ፣ ማኑፋክቸሪንግ በ12.0 በመቶ፣ ኮንስትራክሽን በ12.3 በመቶ፣ አገልግሎት ደግሞ በ7.1 በመቶ የሚያድጉ መሆናቸው ተገምግሟል።

ያለፉት 9 ወራት ጠቅላላ የመንግሥት ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ134 በመቶ ብልጫ አሳይቷል። የውጭ ብድር ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ ወደ 13.7 በመቶ ወርዷል። ወደ ውጭ ገበያ የሚቀርቡት ስድስት ዋና ዋና ምርቶች፣ ካለፈው ዓመት ጋርሲነጻጸሩ ከ82 በመቶ እስከ 386 በመቶ ጭማሪ አሳይተዋል። በስንዴ፣ በሩዝ፣ በቡና፣ በሻሂ ቅጠል እና በፍራፍሬ ምርቶችበአፍሪካ ቀዳሚ ሆኖ ለመውጣት እየተደረገ ያለው ትግል ፍሬ እያፈራ መሆኑን አይተናል።

ውድ የብልፅግና አመራሮች፣ የብልፅግና አባላትና መላው ሕዝባችን፣

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ዝቅተኛ ኑሮ በሚኖሩ ወገኖችላይ ጫና እንዳያሳድር አስፈላጊ የሆኑ እና የታቀዱ የድጋፍ መርሐግብሮች መከናወናቸውንም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው መርምሯል። ለማዳበሪያ 62 ቢሊዮን ብር፣ ለሴፍቲኔት 41.2 ቢሊዮን ብር፣ ለነዳጅ 60 ቢሊዮን ብር፣ ለመድኃኒት 3.5 ቢሊዮንብር፣ ለምግብ ዘይት 6.1 ቢሊዮን ብር፣ እንዲሁም ለደመወዝ 38.4 ቢሊዮን ብር ድጎማ ተደርጓል። ባለፉት 9 ወራት ብቻ 344,790 የውጭ ሀገር ሕጋዊ የሥራ ዕድሎች እና ከ3 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ የሥራ ዕድሎች ተፈጥረዋል።

የርቀት የሥራ ዕድሎች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱ ታይቷል።

የመንግሥት የልማት ተቋማትን በአዲስ አስተሳሰብ እና በአዲስ መንገድ መልሶ ለማደራጀት እና ለመምራት መቻሉ፣ እያስገኘውያለው ውጤት ለሌሎች አርአያ የሚሆን እንደሆነ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ገምግሟል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አሁን ያለው ጠቅላላ ገቢ 1.5 ትሪሊዮን መድረሱ ታይቷል። ከባለፈው ዓመት የ9 ወራት አፈጻጸም አንጻር የዘንድሮ ገቢው የ86 በመቶ ጭማሬ ማሳየቱም ተረጋግጧል። ይሄም መንግሥት የሀገርን ሀብት ለማወቅ፣ ዐውቆም በሚገባ ለማስተዳደር፣ አስተዳድሮም ወረት ለማከማቸት የተከተለው መርሕ ትክክል መሆኑን አረጋግጧል።

የውጭ ምንዛሬ ክምችት ዕድገት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ 9 ወራት ጋር ሲነጻጸር የ203.99 በመቶ ዕድገት አሳይቷል። የባንኮች ተቀማጭ ገንዘብ ከ3 ትሪሊዮን በላይ ተሻግሯል። የ9 ወራት የወጪ ንግድ አፈጻጸም ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሲሆን፣ ይሄም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ150.39 በመቶ ዕድገት አምጥቷል። ባለፉት ስምንት ወራት 473.9 ቢሊዮን ብር ብድር ከንግድ ባንኮች ተለቅቋል። ይሄም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አንጻር በ61.9 በመቶ ከፍ ይላል። ከዚህ ብድር ውስጥም 76.6 በመቶ ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ ነው። ለግሉ ዘርፍ የበለጠ ብድር መሰጠቱ፣ የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ተገቢውን ሚና እንዲጫወት ያስቀመጥነው ፖሊሲ በተግባር እየተገለጠ መሆኑን አመላካች ነው።

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት የጀመርናቸው ሁሉን አቀፍ ጥረቶች ፍሬያቸው እየጎመራ ነው። የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች 50.2 ሚሊዮን፣ የሞባይል ተጠቃሚዎችም 86.6 ሚሊዮን ደርሰዋል። የቴሌ ብር ደንበኞችም ከ52.56 ሚሊዮንበላይ ናቸው። ዲጂታል ፋይናንስ፣ የኅብረተሰቡን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ ለኢኮኖሚው መሣለጥ ጉልህ ድርሻ እያበረከተ ነው። ባለፉት 9 ወራት በዲጂታል መንገዶች 7.73 ቢሊዮን ብር ተቆጥቧል። 26.77 ቢሊዮን ብር በዲጂታል በኩል ብድር ተሰጠ ሲሆን፣ የ12.51 ትሪሊዮን ብር ግብይትደግሞ በዚሁ መንገድ ተከናውኗል።

ዋና ዋና ፕሮጀክቶችን በጊዜ እና በተገቢ ደረጃ ለማጠናቀቅ የተሰጠው አቅጣጫ ብዙዎችን ለፍጻሜ እያበቃቸው ነው። የሕዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 98.66 በመቶ ደርሷል። የኮይሻ፣ አይሻ እና አሰላ የኃይል ማመንጫዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሠረት እየተጓዙ መሆናቸው ተገምግሟል። የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታም የኢትዮጵያን ነገ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የቅድመ ዝግጅት ምእራፉ እየተከናወነ ይገኛል። የኮሪደር ልማት በአዲስ አበባ በ8 ኮሪደሮች እና በመላው ኢትዮጵያ በ65 ከተሞች እየተከናወነ መሆኑ ተስፋ ሰጪ ነው። ብዙዎቹ የመስኖ ግድቦች ወደ ፍጻሜያቸው እየደረሱ ናቸው። ከዘጠኙ የመስኖ ግድቦችውስጥ ስድስቱ አፈጻጸማቸው ከ75 በመቶ በላይ ደርሷል።

“ትምህርት ለትውልድ” በሚል መሪ ቃል ከ82 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ የተሰበሰበ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 6815 ትምህርት ቤቶች በመላ ሀገሪቱ ተገንብተዋል። የነባር ትምህርት ቤቶችንዐቅም ለማሻሻል እና በግጭት የተጎዱትን ለመጠገንየተደረገው ጥረት በትውልድ ላይ ለሚሠራው ሥራ መሠረትየሚጥል መሆኑ ታይቷል። የወላድ እናቶችን እና የጨቅላ ሕጻናትን ሞት በመቀነስ ረገድ የተሻለ ውጤት መመዝገቡም ታይቷል።

በኢትዮጵያ የቱሪዝም መዳረሻዎችና የስፖርት ሥፍራዎችበቁጥርም፣ በዓይነትም እያደጉ መጥተዋል። በተለያዩከተሞች በመገንባት ላይ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ስታዲየሞችበመጠናቀቂያ ምእራፍ ላይ ናቸው። ይሄም ኢትዮጵያ ታላላቅ አፍሪካዊ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ ለያዘችው ዕቅድ መሳካት ወሳኝ ነው። ከዚህ በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ኩነቶችን ለማስተናገድ ያላት መሠረተ ልማት እናየመስተንግዶ ዐቅም እያደገ ይገኛል። ባለፉት ዘጠኝ ወራትከ66 በላይ ዓለም አቀፍ ኩነቶች በሀገራችን ተደርገዋል።በቱሪስት ፍሰት ጭማሪ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር በመሆን ላይነን። የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊ፣ ታሪካዊ እናሃይማኖታዊ ጸጋዎች አውጥተን ማሳየት ከቻልን፣ በቱሪዝምመስክ የቀዳሚነት ሚና መጫወት እንደምንችል ጅምሮቹያሳያሉ።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተከናወኑ ተግባራት አምራችነትንበማበረታታት፣ ሥራ ያቆሙ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ሥራበማስገባት፣ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት፣የሀገር ውስጥ ገቢን በማሰባሰብ፣ ወጪ ምርቶችን በብዛትበማምረት፣ ከአንድ ጊዜ በላይ መሬትን ደጋግሞ በማረስ፣ሪፎርሞችን በየዘርፋቸው አግባብ በመተግበር፣ የተመዘገቡውጤቶች ተስፋ ሰጪ ናቸው። በዚህ እንቅስቃሴ የተነሣራስን የመቻል ተነሣሽነት ጨምሯል። ዘጠኝ ክልሎችሰብአዊ ድጋፍን በራሳቸው ዐቅም ከመሸፈናቸውም በላይየሰብአዊ ድጋፍ ፈላጊዎች ቁጥርም ባለፉት አምስት ዓመታትበሀገር አቀፍ ደረጃ በ86 በመቶ ቀንሷል። ሂደቱ ተረጂነትንመጸየፍና አምራችነትን ባህል ማድረግ በሀገራችን ሥርእየያዘ መሆኑን አመላካች ነው።

ውድ የብልፅግና አመራሮች፣ የብልፅግና አባላትናመላው ሕዝባችን፣

እነዚህ ስኬቶች የጉዟችን መጀመሪያ እንጂ መጨረሻአይደሉም። ማበረታቻዎች እንጂ ፍጻሜዎች አይደሉም።ስኬቶቹ መንገዳችን ትክክል መሆኑን የሚያሳዩ የተራራ ላይመብራቶች ናቸው። ለበለጠ ሥራ የሚያነሣሡ፣ ለበለጠ ወኔየሚቀሰቅሱ፣ የጠለቀ ቁጭት የሚቆሰቁሱ ናቸው።

በሠራናቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የጸጥታ ተቋማትሪፎርሞች ሀገራችን ከነበረባት የህልውና አደጋ ወጥታ ወደአስተማማኝ ህልውና እየተሻገረች ነው። ሪፎርሙ የነበረውንየህልውና ሥጋት መቀልበስ ብቻ ሳይሆን፣ የሀገርን ህልውናለመጠበቅ የሚያስችል አስተማማኝ ዐቅም ፈጥሯል። ይሄምበተቃራኒው መንግሥትን በኃይል ለመጣል የነበረውን ፍላጎትአምክኗል።

በተደረጉ ሀገር በቀል ማሻሻያዎች፣ በተፈጠረው ዐቅም እናዝግጁነት ኢኮኖሚያችን ወደ ተሟላ የኢኮኖሚ ማሻሻያትግበራ ገብቷል። ይሄ ደግሞ የኢኮኖሚ ሂደታችንን እናየብልፅግና ጉዟችንን የሚቀይር አዲስ ምእራፍ ፈጥሯል።የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ እና የባሕር በር ጉዳይ በቀጣናችንየአጀንዳ የበላይነት እንድንፈጥር አስችሎናል። በዚህምየተነሣ ሀገራችንን ከተከላካይነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነትአሸጋግሯታል። በመሆኑም ለውጡ ከመተከል ወደማንሠራራት ተራምዷል ማለት ይቻላል።

መንግሥት የፈጠረው ዐቅም፣ የፀረ ለውጥ ኃይሉ መዳከምእና ዓለም አቀፍ ለውጡ የኢትዮጵያን ሪፎርም ለማሳካትየተሻለ ዕድል የሚሰጥ ነው። መንግሥትን በኃይል ለመጣልናፍላጎትን በጉልበት ለማሳካት የሚደረገው መፍጨርጨርውጤት እንደማያስገኝ ሀገራዊ እውነት እየሆነ ነው።በየጊዜው ወደ ሰላም የሚመጡት ታጣቂዎች ቁጥርመጨመርም ይሄንን ያመለክታል።

በአንድ በኩል እነዚህን ስኬቶች ይበልጥ ማስፋትና ማጽናትአለብን። በሌላ በኩል ደግሞ ራሳችንን ከመሐል ዘመንወጥመድ መጠበቅ ይገባናል። የመሐል ዘመን ወጥመድ፣አንድ ሀገር ከፖለቲካ ሥርዓት ሽግግር በመውጣት፣ ወደቀጣዩ የማጽናት ምእራፍ ከመድረሷ በፊት፣ በሚገኘውየመሐል ዘመን፣ በስኬቶች ረክቶና ተዘናግቶ የመቀመጥአባዜ ነው። ከፖለቲካ ሽግግር በመውጣትና የጸና ሥርዓትንበመትከል መካከል የሚገኝ ፈታኝ ዘመን ነው።

የሀገራችን ኢኮኖሚ በማደግ ላይ ያለ እንጂ በሚፈለገውመጠን ያደገ አይደለም። በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በከተማልማት፣ በወጪ ምርቶች፣ በማዕድን፣ በአገልግሎት ዘርፍ፣በዲጂታል ኢትዮጵያ፣ ወዘተ. ያየናቸው ለውጦች ብንሠራየት እንደምንደርስ አመላካቾች ናቸው። ከግባችንመድረሳችንን ግን አያበሥሩም። የፖለቲካ ባህላችንእየተለወጠ ነው፤ ነገር ግን የሠለጠነ የፖለቲካ ባህል ገናአልገነባንም። የጸጥታ ተቋሞቻችን እየዘመኑና እየደረጁናቸው፤ ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ልክ ገና አልደረሱም።የፖለቲካ ፍላጎትን በኃይል የማስፈጸም አካሄድ ፋሽኑእያለፈበት መጥቷል። ነገር ግን ገና ከፖለቲካና ከማኅበራዊባህላችን ተፍቆ አልጠፋም። የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ገናበጅምር ላይ ነው። ዕዳችን ቢቃለልም ገና ከጫንቃችንፈጽሞ አልወረደም። የዋጋ ግሽበትን ብንቋቋመውም፣ የኑሮውድነትን ግን በተገቢው መንገድ ገና አላቃለልነውም።

በመሆኑም ከስኬት ማማ ላይ የደረስን መስሎን፣ በመሐልዘመን ወጥመድ እንዳንያዝ አመራሮችና አባላት ነቅተውእንዲታገሉ፣ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በአጽንዖት ያሳስባል።

የመሐል ዘመን ወጥመድ በዋናነት የሚከሠተው በውጤትበመዘናጋት፣ ችግርን በመላመድ፣ ሀገራዊ ዕይታን ትቶ በጎጥውስጥ በማደር እና የሕዝብን ችግሮች በጊዜያቸውናበልካቸው ባለመፍታት ነው። በመሆኑም እነዚህ ችግሮችየመሐል ዘመን ወጥመድን እንዳያመጡብን በአመራሩናበአባላቱ ዘንድ ትግል ሊደረግባቸው ይገባል።

ውድ የብልፅግና አመራሮች፣ የብልፅግና አባላትናመላው ሕዝባችን፣

የተዛባ ትርክት እንዳይፈጠር የብሔራዊ ዐርበኝነት ትርክትን በሚገባ ማሥረጽ ይጠበቅብናል። የሕዝብን ጥያቄዎች በየደረጃው መፍታት አለብን። ምርትና ምርታማነትን ከፍ በማድረግ የኑሮ ውድነትን የሚያቃልሉ ሥራዎችን መሥራት ይጠበቅብናል። የተጀመሩ ኢኒሼቲቮችን የሕዝብ ርካታበሚፈጥሩ መልኩ ወደ ውጤት ማድረስ አለብን። ከጠላቶቻችንን ላይ የመሣሪያም የትርክትም ትጥቅ ማስፈታት ይገባል። ለጠላት ተጋላጭነትን ሊፈጥሩ የሚችሉ አሠራሮችን ማረም ጊዜ የማይሰጠው ተግባር ነው። የአመራር ሥምሪትን መፈተሽና ማጥራት መንገዳችንን የበለጠ ምቹ ያደርገዋል። ትጋትና ቁርጠኝነትን መጨመር፣ መናበብን እና ቅንጅትን ማሣለጥ አለብን።

ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚፈጥሩ፣ ገዥ ትርክትን የሚያሠርጹ፣ ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን የሚያስከብሩ እና የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያረጋግጡ ተግባራትን ባለማሰለስ በየአካባቢያችን ተግተን ማከናወን ያስፈልገናል።

የክረምት የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን በተገቢ ዕቅድ እና ቅንጅትመርተን ለውጤት ማብቃት ይገባናል። በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በዚህ ዓመት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ሕዝቡን የማትጋት እና የማሳተፍ ሥራ ከአሁኑ መጀመር አለበት። ለመኸር የእርሻ ሥራዎች የሚያስፈልጉ ግብዓቶች እና ማሽነሪዎች በተገቢ ቦታና ጊዜ እንዲደርሱ የአመራር ሚናችንን እንወጣ። አንድም መሬት ጦም በማያድርበትሁኔታ የግብርና ሥራዎች እንዲከናወኑ እናድርግ።

በአጠቃላይ፣ በሰላማዊ እና በሠለጠነ መንገድ ልዩነቶቻችን በመፍታት፣ የጀመርናቸው ሪፎርሞች በማሳካት፣ የገጠሙንን ፈተናዎች በጽናት በማለፍ፣ ተግዳሮቶቻችንን በመጋፈጥ እና በማሸነፍ፣ የኢትዮጵያን ብልፅግና እውን እንድናደርግ፣ የብልፅግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለብልፅግና ፓርቲ አመራር እና አባላት፣ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ለመላው የኢትዮጵያሕዝብ ጥሪ ያቀርባል።

የብልፅግና ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

ሚያዝያ 18/ 2017፤ አዲስ አበባ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *