ብልፅግና ፓርቲ ካካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው በኋላ አያሌ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች ማስመዝገቡን የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ዛሬ ባውጣው መግለጫ አስታወቀ።
የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሚያዝያ 17 እስከ 18/2017 ዓ.ም ያካሄደውን መደበኛ ስብሰባውን መጠናቀቅ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫውም ከተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በየደረጃው የሚደረገው ምክክር እና ትብብር በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ወደ አዲስ ምዕራፍ መግባቱን ተጠቅሷል።
ከአንድ ክልል በስተቀር፣ ለሀገራዊ ምክክር አጀንዳ የማሰባሰብ ምዕራፍ በሁሉም ክልሎች መጠናቀቁን ነው የገለጸው።
በሀገሪቱ የፀጥታ ችግር በነበረባቸው አንዳንድ አካባቢዎችም ሰላም እየሰፈነ እንደሆነ የጠቀሰው መግለጫው፣ መንግሥት በተደጋጋሚ ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ እጅ የሚሰጡ እና ወደ ሰላም ድርድር የሚመጡ ታጣቂዎች ከዕለት ወደ ዕለት ቁጥራቸው እየጨመረ እንሚገኝ አስታውሷል።
የመንግሥት ሕግ የማስከበር እና የማድረግ ዐቅም እየጎለበተ መምጣጡንም ሥራ አስፈጻሚው አስታውቋል።
EBC


