በዲፕሎማሲው ዘርፍ የተገኘው ስኬት ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ተፈላጊ እንድትሆን እንዳስቻላት የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አስታወቀ።
ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ከሚያዝያ 17 እስከ 18/2017 ዓ.ም ያካሄደውን መደበኛ ስብሰባውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ዛሬ ባውጣው መግለጫ፣ ከሶማሊያ ጋር ተፈጥሮ የነበረው ውዝግብ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፈታቱን ገልጿል።
ኢትዮጵያ የባሕር በር እንዲኖራት የተያዘው አቋም ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነቱ እየጨመረ መምጣቱ ነው በመግለጫው የተብራራው።
ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ያላት ግንኙነት ከመሻሻሉም በላይ የሚደረግላት ድጋፍ እያደገ መምጣቱ ሌላው የዲፕሎማሲ ስኬት መሆኑን ሥራ አስፈጻሚው አስታውቋል።
በዓለም አቀፍ መድረክ የኢትዮጵያ ተፈላጊነት መጨመሩ የዲፕሎማሲው ስኬት ማሳያ መሆኑን የጠቀሰው ሥራ አስፈጻሚው፣ የዲፕሎማሲ ግንኙነቷ በሁሉም አቅጣጫ ከፍ እንዳለ ገልጿል።
EBC


