የልማት ድርጅቶችን በአዲስ አስተሳሰብና መንገድ መልሶ በማደራጀት ለመምራት በመቻሉ እመርታዊ ለውጥ መጥቷል፡- የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

የንግድ ባንኮች ባለፉት ስምንት ወራት ከሰጡት 473.9 ቢሊዮን ብር ብድር ውስጥ 76.6 በመቶ የሚደርሰው ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አስታውቋል።

ይህም የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ተገቢውን ሚና እንዲጫወት የተቀመጠው ፖሊሲ በተግባር እየተገለጠ ስለመሆኑ አመላካች ነው ብሏል ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ዛሬ ባወጣው መግለጫው።

የውጭ ምንዛሬ ክምችት ዕድገት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ 9 ወራት ጋር ሲነጻጸር የ203.99 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ያለው ኮሚቴው፤ የባንኮች ተቀማጭ ገንዘብም ከ3 ትሪሊዮን በላይ መድረሱንም አክሏል።

የመንግሥት የልማት ተቋማትን በአዲስ አስተሳሰብና በአዲስ መንገድ መልሶ በማደራጀት ለመምራት መቻሉ እና ይህም እያስገኘው ያለው ውጤት ለሌሎች አርአያ የሚሆን ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አሁን ያለው ጠቅላላ ገቢ 1.5 ትሪሊዮን መድረሱን የጠቀሰው ኮሚቴው፤ ከባለፈው ዓመት የ9 ወራት አፈጻጸም አንጻር ሲታይ የዘንድሮ ገቢው የ86 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱምን አክሏል።

ይህም መንግሥት የሀገርን ሀብት ለማወቅ፣ አውቆም በሚገባ ለማስተዳደር፣ አስተዳድሮም ወረት ለማከማቸት የተከተለው መርሕ ትክክል መሆኑን አረጋግጧል ብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *