” የድሬዳዋ ፖሊስ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተቋም እንዲሆን ሚናችሁ ከፍተኛው ነበር “፡- የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዣዥ ክቡር ኮምሽነር አለሙ መግራ
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የስራ ጊዜያቸው ላጠናቀቁት የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚዎች የምስጋናና የክብር ሽኝት መርሀ ግብር አካሄደ ፡፡
በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሐር፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ፣ በፌደራል ፍትህ ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ቃሲም አማን እንዲሁም የዘርፍ ኃላፊዎች ፣ የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የወረዳው ማ/አ/ፖሊስ ምክር ቤት ተወካዮች እንዲሁም የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ የምክር ቤት ስራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዋል ፡፡
በምክር ቤቱ የስራ አስፈፃሚዎች የምስጋናና የክብር ሽኝት መርሀ ግብር ላይ ተኝተው መልክታቸውን ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሐር እንደተናገሩት የስራ ጊዜቸውን ያጠናቀቁት የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚዎች አመራሮች ባለፉት አመታት የድሬዳዋ ከተማን ሰላም ፀጥታ በማስጠበቅና ሰላሙን በበላይነት በመምራት ነገን የተሻለ ድሬዳዋ ለመገንባት ያለምንም መታከት ጊዜና ጉልበታችሁን በመስጠት በበጎ ፍቃድኝነት ላበረከታችሁት አስተዋፅዖ ምስጋና እንደሚገባ ገልፀው በቀጣይም አዲሱን የምክር ቤት ስራ አስፈፃሚዎች ልምዳችሁን በማጋራት እንደሚጠበቅባችሁና ይህን በማድረጋችሁ በአስተዳደር ደረጃ ትልቅ ኩራት እንደሆነ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ጨምረዉ ገልፀዋል ፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ኮምሸር አለሙ መግራ እንደተናገሩት የማህበረሰብ አቀፍ ምክር ቤቱ ባለፈው አመታት ባከናወናቸው ጠንካራ ስራዎች የድሬዳዋ ፖሊስ የተሻለ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተቋም እንዲሆን የስራ አስፈፃሚዉ ሚና ከፍተኛ ነበርና ፖሊስን ከማህበረሰብ ጋር ድልድይ በመሆን በማድረጋችሁ ከዚህ ቀደም ይፈፀሙ የነበሩ ወንጀለኞች እንዲቀንስ ከማድረጉም ባሻገር የድሬዳዋ ፖሊስ በሚፈለገው መስመር እንዲጓዝ በማድረግ ልምዳችን በማካፈል ላበረከታችሁት ስራ ትልቅ ኩራት ሊሰማችሁ ይገባል ሲሉ ኮምሽነር አለሙ መግራ ጨምረው ተናግረዋል ።
በመድረኩ ላይ ባለፉት አመታት በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ም/ቤት ተከናወኑ ስራዎች በጠቅላይ መምሪያው የማህበረሰብ አቀፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ትዕግስት ተሾመ ተከናወኑ ስራዎችን ሪፖርት በዝርዝር ቀረበ ሲሆን
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ምክር ቤት በደንቡ መሰረት አዲስ የምክር ቤት ስራ አስፈፃሚ ምርጫ ያካሄደ ሲሆን በዛሬው ዕለት የቀድሞ የስራ አስፈፃሚ አባላት ባለፉት አመታት ለድሬዳዋ ከተማ ሰላምና ደህንነት ላበረከቱት አስተፅኦ በመድረኩ የክብር ሽኝት የተካሄደ ሲሆን በወቅቱም የምስጋና የምስክር ወረቀት ፤ሜዳልያ፣ ዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል በክብር ተሸኝተዋል ፡፡


