የድሬዳዋ አስተዳደር አመራሮች እና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ተወያዩ።

<<የመሃሉ ዘመን!>>በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ አስተዳደር የሴክተር እና ወረዳ አመራሮችና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ የተወያዩ ሲሆን የውይይቱ ዋንኛ አላማም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባለፉት ተከታታይ 7 አመታት ለውጡን ለማፅናት በተደረጉ ጥረቶች፣ የተገኙ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ውስጣዊ፣ ቀጠናዊና አለም አቀፋዊ ተግዳሮቶችና የተወሰዱ እርምጃዎች እንዲሁም አሁናዊ ሀገራዊ ሁኔታና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በተመለከት ሰራተኞችና አመራሮች የጠራ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና በቀጣይም እንደሀገር ሊገጥሙ የሚችሉ ፈተናዎችን በሚገባ መቀልበስ የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ መሆኑ ተገልጿል።

ሁሉም አመራር እና ሰራተኛ በተለይ በአገልግሎት ዘርፍ የተሻለ ለውጥ እንዲመጣ በመረባረብ የተጀመረውን ለውጥ በማፅናት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም በሁሉም መድረኮች መልዕክት ተላልፈዋል።

በመድረኩ <<የመሃሉ ዘመን!>>በሚል መሪ ቃል ለውይይት መነሻነት የሚሆን ሰነድ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገበት ሲሆን አመራሮች እና ሠራተኞች ወቅታዊ ሀገራዊ ፣ ቀጠናዊ፣ አህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ወቅታዊ የሆነ መረጃ ሊኖራቸው እንደሚገባና በዚህም ሀገራዊ ለውጡን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማደናቀፍ የሚጥሩ ማናቸውንም ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ ኃይሎችን በመጋፈጥ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *