የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ያለውን ሀገራዊ ፋይዳ በመረዳት ሁሉም ማህበረሰብ እንዲመዘገብ ጥሪ ቀረበ

በድሬዳዋ አስተዳደር የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በየተቋማት እየተካሄደ ሲገኝ፤ በዛሬው ዕለትም በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ፈት ቤት ምዝገባው ተጀምሯል፡፡

በዚህም ምዝገባውን ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ አብዱለዚዝ ሻፊ የዲጂታል መታወቂያ ህዝባዊ አገልግሎቶችን በማቀላጠፍ የዜጎችን የጤና እና የትምህርት ደረጃ መረጃ በማገናዘብ ፎርጅድ እና አጠቃላይ ህገ ወጥነትን ለመከላከል ወሳኝ ሚና ያለው መሆኑን አመላክተዋል።

አቶ አብዱለዚዝ አክለውም ሁሉም ማህበረሰብ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ያለውን ሀገራዊ ፋይዳ በመረዳት እንዲመዘገብ ጥሪ አቅርበዋል።

በምዝገባው ወቅት ያነጋገርናቸው ሰራተኞች በበኩላቸው ሀገራችን ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በምታደርገው ጉዞ የ‘ፋይዳ’ ዲጂታል መታወቂያ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:-ሰላም አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *