የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ለሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል ።
በዛሬው እለት በነበረው የስልጠና መርሀ-ግብርም ስማርት ሲቲን መገንባት ብሎም ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት በቴክኖሎጂ ማበልፀግ እንደሚገባና በተለይም የአስተዳደሩ መሬት ልማት ፣ ገቢዎች ባለስልጣን እንዲሁም ፖሊስ ኮሚሽን አሰራራቸውን በቴክኖሎጂ ማበልፀግ መቻላቸው ለተገልጋዩም ማህበረሰብ ቀልጣፋ የሆነ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉም በእጅጉ እንደሚረዳም ነው የተገለፀው ።
ሌሎች ተቋማትም አገልግሎታቸውን በቴክኖሎጂ የታገዘ ከማድረግ ጋር ተያይዞ ጅምር ስራዎች እየተሰሩ እንዳሉና ነገር ግን የተጀመሩት ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው አገልግሎታቸውን በቴክኖሎጂ በመታገዝ መስራት እንደሚገባቸውም ነው የተገለፀው ።
በአለማየሁ አበበ
ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋረጋ


