በአፍሪካ እና በሌሎች የአለም አገራት ከሚገኙ እህት ከተሞች ጋር ወዳጅነት በመፍጠር፥ ለድሬ ሁለንተናዊ እድገት መፋጠን የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን ቀጥለናል።

በማዳጋስካር ዋና ከተማ አንታናናሪቮ ከንቲባ ሃሪላላ ራማንትሶአ የተመራ ልዑክ ቡድን፥ ለሁለት ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር ያደረገው ጉብኝት እና ውይይት የዚህ ጥረታችን አንዱ አካል ነው።

ክብርት ከንቲባዋ እና ልዑካቸውን እንዲሁም የ’ትንሿ ኢትዮጵያ’ ድሬ አምባሳደር የሆነችው ውድ እህቴ ገነት ወ/ስላሴን ከልብ እያመሰገንኩኝ፥ በቀጣይ ከማዳጋስካሯ አንታናናሪቮ ከተማ ጋር በተለያዩ የልማት ዘርፎች በትብብር ለመሥራት፥ አስተዳደራችን ቁርጠኛ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *