የታዳሽ ሀይል ቴክኖሎጂ ለዜጎች ስራ መፍጠሪያ ብሎም ሀብት ማፍሪያ መሆን የሚችል ዘርፍ መሆኑ ተገለፀ

የድሬዳዋ የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከየአርዳ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በዘርፉ ትምህርትና ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ተገልፆዋል።

ADRA ፕሮጀክት የ5000 ዋት solar PV system installation and commissioning ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የድሬደዋ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በአስተዳደሩ ስራ አጥነትን ለመቅረፍ በሚደረገው ጥርት ወጣቶችን ስልጠናውን እንዲወስዱ እየተደረገ ይገኛሉ ብለዋል።ፕሮጀክቱ በተለይም የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌትሪክ ሀይል ተጠቃሚ ከማድረግ ጎን ለጎን ወጣቶችን በማደራጀት የስራ እድል ተጠቃሚ አንዲሆኑ ያደርጋል ሲሉ ገልፀዋል።

በኮሌጁ ሰልጥነው ለሚመረቁ ተማሪዎች የስራ እድል ትስስርን ከመፍጠር አኳያ ከየተቋማት ጋር በጋራ በመስራት ላይ መሆኑን የቢሮ ሃላፊው ጠቁመዋል።

በቀጣይ ድሬዳዋን ስማርት ሲቲ ላመድረግ በሚሰሩ ስራዎችም ሆነ በተለያዩ ዘርፎች የሶላር ኢነርጂ በስፋት ጥቅም ላይ የማዋል ሁኔታ ስለሚኖር ከወዲሁ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሃይል ለማፍራት የአድራ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር በማስቻሉ በአስተዳደሩ ስም አቶ ሮቤል ምስጋና አቅርበዋል።

በሌላ በኩል የአድራ ኢትዮጵያ የፕሮግራም ዳይሬክተር ዶክተር ዘሪሁን አዋኑ አርዳ ፕሮጀክት ሁለት ዋና ዋና ሰበአዎነትን መሰረት ያደረጉ ስራዎችን ማለትም የነብስ አድንና የህይወት መለወጥ(ላይፍ ሴቪንግ ኤንድ ላይፍ ቼንጂግ) እንደሚያከናውን ገልፀዋል።

አርዳ ከኮሌጁ ጋር በመተባበር ባለፉት 2 አመታት 90 ወጣቶችን በዘርፉ ማሰልጠናቸውን ገልፀው ፕሮጀከቱ ሰልጣኞች በዘረፉ በቂ እውቀት እንዲጨብጡ እንዲሁም የራሳቸውን ስራ እንዲፈጥሩ ያደረገል ብለዋል።

ድሬዳዋ ለሶላር ሃይል ቴክኖሎጂ ምቹ እነደሆነች ቴክኖሎጂውን በበቂ ሁኔታ መጠቀም ከተቻለ የስራ እድል በመፍጠር የላቀ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው አስረድተዋል።

ፕሮጀክቱ በድሬዳዋ አስተዳደር መተግበር ከጀረ ጀምሮ እስካሁን የታየው ውጤት አበረታች እንደሆነ፣በተለይ ኮሌጁም ሆነ በአስተዳደሩ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በትብብር የመስራት ስሜት በመኖሩ በቀጣይም የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚቻል አስረድተዋል።

አቶ ታደለ አሰፋ የኢትዮጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን

ፕሮጀክቱ በርካታ ያለተዳሰሱ አቅሞችን መጠቀም ያስቻለ እየሆነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ኮሌጁ በሶላር ኢነርጂ ዘርፍ በከተማና በገጠር የሚገኙ ተማሪዎችን እያሰለጠነ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በመጀመሪያ ዙር 48 ወጣቶች በሶላር ቴክኖሎጂ ሰልጥነው ከመመረቅ ባለፈ የሙያ ምዘና ወስደው ሰርቲፋይድ መሆናቸውን፣ በሁለተኛ ዙር 43 ወጣቶች በመስኩ ስልጠና እየወሰዱ መሆናቸውን ጠቁዋል።

ፕሮጀክቱ የመምህራንን አቅም ከመገንባት እንዲሁም የተለያዩ ግብአት በማሟላት ጭምረ አስተዋፅዖ ማድረጉን አቶ ታደለ አስረድተዋል።

አርዳ ኢትዮጵያ 5.5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 5ሺህ ዋት የሚያመነጭ የሶላር ሃይል የሚየመነጭ ፓኔል ተገንብቶ ለድሬደዋ ኢትዮጣሊያን ኮሌጅ አሰወረክቧል።

በዳግማዊ ፍቃዱ

ፎቶ፦በዳዊት መስፍን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *