ማዳጋስካር ዋና ከተማ አንታናናሪቮ ከንቲባ ሀራላላ ራማናቶሳ የተመራው ልኡካን ቡድን በድሬዳዋ እያከናወነ የሚገኘው ጉብኝት ቀጥሎ ልኡክ ቡድኑ በዛሬው ዕለት ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ እንዲሁም በመስተዳደሩ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን የድሬዳዋን ነፃ የንግድ ቀጠና፣ ደረቅ ወደብን፣አዲሱ ምድር ባቡርን እንዲሁም ሀሴት የህክምና መገልገያ እቃዎች ማምረቻን በመመልከት ልኡኩ በቬራ ፖስታ መንገድ በኮሪደር ልማት በለማው ስፍራ የባቡር ሽር ሽር አድርገዋል።
በዚህም እንግዶቹ ከድሬዳዋ በርካታ ልምዶችን መቅሰማቸውን ገልፀው በተለይም ከተማዋ በኢንደስትሪውና በማኒፋክቸሪንጉ ዘርፍ እየሰራች ያለችው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል። የሁለቱ ከተሞች ትስስርም በቀጣይም እንደሚጠናከር አመላክተዋል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-ቴድሮስ ልዑልሰገድ


