የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በድሬዳዋ የገበያ ማእከላት ተወካዮችና የንግድ ድርጅቶች ባለቤቶች ጋር የኢትዮጵያ ብሐቤራዊ መታወቂያ “ፋይዳ”ተመዝግበው በመያዝ ዲጅታል መታወቂያው የሚያስገኛቸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን እንዲያገኙ ለማስቻል ባዘጋጀው የንቅናቄ መድረክ ላይ ተወያይተዋል

የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሐመድ የድሬዳዋ አስተዳደር ለየት ባለ ሁኔታ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያን ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር ከሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ግንባር ቀደም የሚያደርጋትን ስራ በማከናወን ላይ መሆኗን ጠቅሰው ፣ የንግዱ ማህበረሰብ ዲጂታል መታወቂያውን ከሚያዚያ እስከ ሰኔ 2017 ዓ/ም ድረስ አስተዳደሩ በሚያዘጋጃቸው የመመዝገቢያ ማእከላት ተመዝግበው ሙሉ ለሙሉ መታወቂያውን መያዝ የሚያስችል ንቅናቄ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም እንደ ሀገር ሲሰራበት የነበረው የማንነት መግለጫ መታወቂያ የነበሩበትን በርካታ ችግሮች ለመቅረፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ መንግስት የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ስርዓት መዘርጋቱን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አብዱሰላም ፣እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር መንግስታዊ እና የግል ድርጅቶች የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች በሙሉ ከፋይዳ መታዊቂያ ጋር እንዲተሳሰሩ የሚደረግ በመሆኑ ለመዝገባ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የንግዱ ማህበረሰብ ተመዝግቦ በመያዝ ለንግድና ግብይት ስርዓቱ መዘመን፣ ቅልጥፍና እንደዚሁም የተለያዩ የማጭበርበር ተግባሮችን መከላከልና ማስቀረት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ያዊ አሰራር ነው ብለዋል፡፡

በንቅናቄ መድረኩ ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂ እና በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ የተጀመረው የቀበሌ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ጋር ተያይዥነት ያላቸው የአሰራር ክፍተቶችን እንደዚሁም ሊብራሩላቸው የሚፈልጓቸውን ጥያቄዎች አንስተው ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠባቸው ሲሆን የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮችና የድርጅት ባለቤቶች በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ምዝገባውን እንደሚያጠናቅቁ መግባባት ላይ ተደርሷል ፡፡

በዳንኤል አማረ

ፎቶ ፦ ናታን ሽዋንግዛው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *