በድሬዳዋ አስተዳደር ወረዳ 02 ባርገሌ አካባቢ በህዝብ ተሳትፎ የሚሰራ የጠጠር መንገድ ስራ ማስጀመሪያ መርሀግብር ተካሄደ ።

በድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ልማትና ህብረተሰብ ተሳትፎ ኤጀንሲ እና በወረዳ 02 አስተዳደር ፅህፈት ቤት በጋራ በመሆን የባርገሌ አካባቢ በህዝብ ተሳትፎ የሚሰራ የጠጠር መንገድ ስራ ማስጀመሪያ መርሀግብር ተካሄደ ።

የባርገሌ አካባቢ ህብረተሰብ የበርካታ አመት ጥያቄ የሆነዉ 1 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ከጎሮ ሀዲድ ሀና ግሮሰሪ እስከ ባርገሌ ታክሲ ማዞሪያ ያለዉ መንገድ እንዲሁም የዉሃ መዉረጃ ቦይ ዲች ስራ እዉን ሆኖ በህብረተሰቡ ተሳትፎና በመንግሥት ጥምረት የጠጠር መንገድ ስራ ማስጀመሪያ መርሀግብር ተካሂዷል ።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በማስጀመሪያ መርሀግብሩ ላይ ተገኝተው ፕሮጀክቱ የህዝብን ተሳትፎና አቅም ከመንግሥት ጋር በማቀናጀት ምን አይነት ዉጤት ማምጣት እንደሚቻል ያሳየ መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይም ህዝባችን የሚጠይቀዉን ጥያቄዎች በአግባቡ እንዲመለሱ እናደርጋለን ብለዋል ።

የአካባቢ ልማትና ህብረተሰብ ተሳትፎ ኤጀንሲ ሀላፊ ረሂማ አወል በበኩላቸው ስራዉ ገና ጅማሮ መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይ ፕሮጀክቱ ተሰርቶ እስኪጠናቀቅ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።

የወረዳ 02 ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ አቤል ምስራቅ እንዲሁም ፕሮጀክቱ ህብረተሰቡ መንግስት ላይ እምነት እንዲኖረው ያደረገና የመጣውን ለዉጥ በተግባር የሚያሳይ ነዉ ብለዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *