4ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ተጠናቀቀ

“ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች” በሚል መሪ ሐሳብ ሲካሄድ የነበረው 4ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የማጠናቀቂያ መርሐ-ግብር ተካሂዷል፡፡

በውድድሩ 1ኛ የወጡ ተወዳዳሪዎች 500 ሺህ ብር፣ 2ኛ ለወጡ 400 ሺህ ብር እንዲሁም 3ኛ ለወጡ 300 ሺህ ብር ተሸልመዋል፡፡

ከድሬዳዋ አስተዳደርም በክህሎት፣ በቴክኖሎጂ እና በተግባራዊ ጥናትና ምርምር አሰልጣኝ መምህራን፣ ሰልጣኝ ተማሪዎች እና ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ ሆነዋል።

በውድድሩም ሰልጣኝ ተማሪ ዮሐንስ ሞላ በሀርድዌር እና ኔትወርኪንግ ሰርቪስ መስክ ተወዳድሮ አንደኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳልያ እና የ500 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል ለዚህም በተገኘው ውጤት የአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *