በድሬዳዋ አስተዳደር የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በየተቋማት እየተካሄደ ሲገኝ፤ በዛሬው ዕለትም በሳቢያን የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ምዝገባው ተጀምሯል፡፡
በዚህም ምዝገባውን ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ አብዱለዚዝ ሻፊ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ታማኝነትን የሚዘረጋ፣ የተቋማትን ሥራ የሚያቀናጅ፣ በግለሰቦች ደረጃም የራስን መብት የሚያስጠብቅ መሆኑን አመላክተዋል።
አቶ አብዱለዚዝ አያይዘውም ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የሀገርን እና የዜጎችን ደኅንነት በማስጠበቅ ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለው በመናገር፤ ዜጎች በብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ መስጫ ማዕከላት በመገኘት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-ሰላም አበበ


