የድሬዳዋ ባህልና ታሪክ ላይ እንዲሁም የባቡር መስመሮቿ ላይ ያተኮሩ ሁለት ፊልሞች ለምርቃት በቁ

የጀርመን ባህል ተቋም (ጎተ) ኢንስቲትዩት ከአውሮፓ ህብረት ጋር በመተባበር የተሰሩ በድሬዳዋ ባህል፣ ታሪክና የባቡር መስመሮቿ ላይ ያተኮሩ ሁለት ፊልሞች በዛሬው ዕለት በድምቀት ተመረቁ።

በዚህም ለምርቃት ከበቁት ፊልሞች መካከል የመጀመሪያው አጭር ፊልም skins የተሰኘ ሲሆን ሂናን መሰረት በማድረግ በድሬዳዋ ከተማ ከመሰራረት፣ የባቡር መስመሮቿ፣ በኪነ ህንፃዎቿ፣ በገበያዎቿ፣ በማህበረሰቡ አለባበስ እንዲሁም ሌሎት የአኗኗር ዘይብዎች ላይ የሚስተዋሉ የባህል ልውውጦች ላይ ያተኮረ ሙከራዊ ዘጋቢ ፊልም ሲሆን በወ/ሪት ረድኤት አዲስም የተዘጋጀ ነው።

ሁለተኛው ደግሞ “ምርጧ ኳስ” የተሰኘ ፊውቸር ፊልም ሲሆን በእስቶሪስ ኦን ዘ ትራክ ሪዝደንሲ ፕሮግራም የተዘጋጀም ነው።

በምርቃት መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የጀርመን ባህል ማዕከል ጎተ ኢንስቲትውት ዳይሬክተር ዶ/ር አንገሊካ ኤደር የአውሮፓ ህብረት ዩኒክ እያሰራ ከሚገኘው የባህል ፕሮጀክት መካከል በድሬዳዋ ላይ ያተኮሩ ሁለቱ አጫጭር ፊልሞች በዛሬው እለት ለምርቃት በመብቃታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፤ ፊልሞቹን ሰርቶ ለማጠናቀቅ የሁለት ወር ጊዜ እንደፈጀም ተናግረዋል።

በመጨረሻም ዶ/ር አንገሊካ በፊልም ስራው ላይ ለተሰማሩ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *