ኢትዮጵያ እየፈጠረችው ያለው የቴክኖሎጂ አቅም የታየበት ኤክስፖ

ላለፉት ሦስት ቀናት “አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ለአፍሪካ ብልጽግና እና ትብብር” በሚል መሪ ቃል በአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከል የተከናወነው የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ተጠናቋል።

ከ15 ሺ በላይ ታዳሚዎች የተሳተፉበት ኤክስፖ ውጤታማ እንደነበር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ ገልፀዋል።

በሁነቱ ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ፍሬያማ የፓናል ውይይቶች መካሄዳቸውንም አያይዘው አንስተዋል።

የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የአፍሪካ ሀገራት የሳይበር ደህንነትን በሉዓላዊነት ደረጃ ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ አመላክተዋል።

በኤክስፖው ላይ አህጉሪቱ በዘርፉ ተቀባይ ከመሆን በመላቀቅ የቴክኖሎጂ ባለቤት የምትሆንበት አስቻይ አሰራር ላይ ያተኮሩ ውይይቶች መደረጋቸውን ገልፀዋል።

ከ100 በላይ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች፣ የመንግሥትና የግል ተቋማት እንዲሁም ስታርትአፖች በኤክስፖው ላይ መሳተፋቸውን ተናግረዋል።

ETEX2025 የቴክኖሎጂ ኤክስፖ የልምድ ልውውጥ የተደረገበት እና ኢትዮጵያ እየፈጠረችው ያለው የቴክኖሎጂ አቅም የታየበት ኤክስፖ መሆኑንም ተመላክቷል

EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *