የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዋች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል
ካብኔው በአለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በታዳጊ ሀገሮች ከተሞች መሰረታዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ማነቆዎች በዘላቂነት ለመቅረፍ እና ከተሞች ቅድመ ፍላጎትን እና ስርአትን ተከትለው እንዲለሙ የከተሞችን የ30 ዓመት የህዝብ ቁጥር እድገት እና የመሬት አቅርቦት ፍላጎት ትንበያ ታሳቢ በማድረግ የማስፋፊያ ፕላን ወደ ስራ መግባታቸው ጊዜው ከሚጠይቃቸው አንገብጋቢ ጉዳዬች ውስጥ አንዱ ነው።
በመሆኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ ሁለተኛ ደረጃ ከተሞች ውስጥ አንዱ በሆነችው በድሬዳዋ አሰተዳደር ይህንን የማስፋፊያ ፕላን ለማዘጋጀት ከ2021 እ.እ.ኤ ጀምሮ እየተደረገ ያለውን ጥረት ዳር ለማድረስ የአስተዳደሩ ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ከኢትዬጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ፣ከከተማና ቤቶች ልማት ሚኒስትር እና ከአስተዳደራችን ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮና ከከተማ ፕላን ኢኒስቲቲዩት ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት የተጀመረው ጥናት ሌሎች ባለድርሻ አካላትን አካቶ የጥናት ስራው ተጠናቆ ወደ ትግበራ እንዲገባ ሲል ውሳኔ አሳልፉል።
የድሬዳዋ አሰተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ


