ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም መርህን ከግብ ለማድረስ በስፖርት የበለፀገ ዜጋን ማፍራት ወሳኝ ነው በሚል መሪ ሀሳብ የ 2017 ዓ.ም የመንግስት እና የግል አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመታዊ የተማሪዎች ስፖርት ውድድር በዛሬው እለት ተጠናቋል ።
ስፖርታዊ ውድድሩም ባለፍት ሁለት ወራት ሲካሄድ የነበረ ሲሆን በዚህም ስፖርታዊ ውድድር ላይም 42 የከተማ ትምህርት ቤቶች በ 8 የስፖርት አይነቶች ከ 4500 በላይ ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል ። አዲሱ ትምህርት ቤት ከለገሀሬ ትምህርት ቤት ባደረጉት የእግር ኳስ ጨዋታ ውድድሩም ፍፃሜውን አግኝቷል ።
አዲሱ ትምህርት ቤት ከ ለገሀሬ ትምህርት ቤት ባደረጉት የፍፃሜ እግር ኳስ ጨዋታም አዲሱ ትምህርት ቤት 4 ለ 2 በሆነ ውጤት ለገሀሬ ትምህርት ቤትን ማሸነፍ ችሏል ። በ 8 የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ ውጤታማ ለሆኑ ትምህርት ቤቶች እና ተማሪዎች እንዲሁም ለውድድሩ መሳካት አስተዋፆ ላበረከቱ አካላት የተለያዩ ሽልማቶችም ተበርክቶላቸዋል ።
በአለማየሁ አበበ
ፎቶ :- በአገኘው ሸዋረጋ


