#DGC ግንቦት 24/2017
በአስተዳደሩ 116ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ የምስረታ በዓል አስመልክቶ የ5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሄደ።
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ
116ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ የምስረታ በዓል አስመልክቶ በቅርቡ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት በጀመረው የነበርዋን የኮሪደር ልማት ላይ በተካሄደ የሩጫ ውድድር ደማቅ የመክፈቻ ፕሮግራም ተጀምሯል።
በሩጫ ውድድሩም ከድሬዳዋ ፖሊስ፣ ከኢፌድሪ አየር ሀይል ከሶስተኛ አየር ምድብ እና ከክልል የተሳተፉበት ሲሆን በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ለተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።
በመክፈቻ መርሀግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ፣ አቶ ደረጀ ጸጋዬ ምክትል የመንግስት ተጠሪ እና በብልጽግና ፖርቲ የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጌቱ ተ/ዮሀንስ ምክትል ኮሚሽነር እና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ፣በየደረጃው የሚገኙ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች የፖሊስ አመራርና አባላት፣ እንዲሁም የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በመርሀ ግብሩም መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ጠቅላይ መምሪያ ኮሚሽን ኮሚሸነር አለሙ መገራ የኢትዮጵያ ፖሊስ ህዝብን በማገልገል ህብረ ብሄራዊነትን የግዛት አንድነትን በማስጠበቅ ኢትዮጵያን ባማሻገር በርካታ መሰዋትነትን ከፍለዋል ።
የኢትዮጵያ ፖሊስ 116ኛ አመት ሲከበርም ፖሊስ ያላፋቸውን ውጣውረዶች ማሳየት በቻ ሳይሆን የለውጡ መንግስት ለጸጥታ ተቋማት በሰጠው ትኩረት በአሰራ፣በአደረጃጀት በቴክኖሎጂ በወቅታዊ ቁመናው ሪፈርም በማድረግ በጸጥታው ዘርፍ ለአፍሪካ ምሳሌ መሆን መቻሉን ተናግረዋል ።የድሬዳዋ ፖሊስም ሪፎርሙን በመተግበር በርካታ ውጤት ማስመዝገብ የቻለበት መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ደረጀ ጸጋዬ ምክትል የመንግስት ተጠሪ እና በብልጽግና ፖርቲ የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊም በበኩላቸው የድሬዳዋ ፖሊስ የአስተዳደሩን ሰላም ና ጸጥታ በማስከበር ረገድ ዘርፈብዙ ስራዎችን መስራቱን ገልጸው በቀጣይም ለሚከናወኑ መርሀግብርም አስተዳደሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል ።
በሩጫ ውድድር ለአሸነፉ አባላትም የሜዳሊያ እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ሰላም ለማ
ምስል፦ አገኘው ሸዋረጋ


