ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
“ከ17ኛው የብሪክስ ጉባኤ አስቀድሞ ከብራዚል ፕሬዝደንት ሉዊዝ ኢናቺዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ተገናኝተን በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል። የዛሬው ውይይታችን በቅርብ እያደገ የመጣውን የሁለቱ ሀገሮቻችንን ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ረገድ አንድ ርምጃ ወደፊት የወሰደን ሆኗል። በተለያዩ ዘርፎች የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስሮቻችንን የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተናል።”


