በድሬዳዋ እየተከናወኑ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራዎች በመጠናቀቅ ሂደት ላይ ይገኛሉ፤ በዚህም በምድር ባቡር መንገድ እየተሰራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ለከተማዋ በውበት ላይ ውበትን ከመጨመር ባሻገር መንገዱ ለነዋሪዎች ምቾትን እንደፈጠረ እንደሚገኝ የድሬዳዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ።
በዚህም አስተያየታቸውን ከሰጡን ነዋሪዎች መካከል ወጣት ሀምዲ መሀመድ የኮሪደር ልማቱ የእግረኛና ተሽከርካሪ እንዲሁም የብስክሌትና አረንጓዴ ስፍራዎችን የያዘ በመሆኑ ከዚህ ቀደም የነበረውን የመጨናነቅ ሁኔታ የቀየረ መሆኑን ተናግሯል።
ልማቱ የድሬዳዋን ከተማ መልካም ገጽታ በማጉላት ለነዋሪዎችና ጎብኚዎች ምቹ እያደረገ እንደሚገኝ የተናገሩት ደግሞ አቶ ተሻለ በየነ ናቸው።
ወጣት ሜሎና ታምራት በበኩሏ የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹና ማራኪ ከማድረጉ ባለፈ ለበርካታ ሰዎች የስራ እድል መፍጠሩን ተናግራለች።


