የድሬዳዋ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ውበት አጉሉቶ ከማውጣቱ ባሻገር የኢንቨስትመንት ማእከልነቷን ያጠናክራል ሲሉ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ
በድሬዳዋ እየተከናወኑ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራዎች በመጠናቀቅ ሂደት ላይ ይገኛሉ፤ በዚህም በምድር ባቡር መንገድ እየተሰራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ለከተማዋ በውበት ላይ ውበትን ከመጨመር ባሻገር መንገዱ ለነዋሪዎች ምቾትን እንደፈጠረ እንደሚገኝ የድሬዳዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ። በዚህም አስተያየታቸውን ከሰጡን ነዋሪዎች መካከል ወጣት ሀምዲ መሀመድ የኮሪደር ልማቱ የእግረኛና ተሽከርካሪ እንዲሁም የብስክሌትና አረንጓዴ ስፍራዎችን የያዘ በመሆኑ ከዚህ ቀደም የነበረውን የመጨናነቅ ሁኔታ…


