የብሪክስ ትብብር እየተጠናከረ ነው – ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን

የብሪክስ ትብብር ጠንካራ እየሆነ መምጣቱን ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ።

ፕሬዚዳንቱ በተንቀሳቃሽ ምስል ለብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች ባስተላለፉት መልዕክት፤ የብሪክስ አባል ሀገራት በጋራ ኢኮኖሚያችንን ልናጠናክር ይገባል ብለዋል።

አክለውም ይህን ለማጠናከር ብሔራዊ ገንዘቦችን እውቅና ሰጥተን እርስ በእርስ መገበያየት አለብን ብለው፤ ለዚህ ማሳያም በ2024 ሩሲያ 90 በመቶ ንግዷን የራሷን እና የሌሎች አጋር ሀገራትን መገበያያ ገንዘብ ተጠቅማ ማድረጓን አንስተዋል።

በቴክኖሎጂ፤ በንግድ፤ በፋይናንስ እና በትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ትብብራችንን ማጠናከር አለብንም ብለዋል ፕሬዚዳንት ፑቲን።

ብሪክስ በፍጥነት እያደጉ ያሉ ሀገራትን ከአፍሪካ፣ ከእስያ እና ከደቡብ አሜሪካ ያካተተ በመሆኑ፤ ጠንካራ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ትብብርን የሚፈጥርም እንደሆነም ነው ያነሱት።

ይህ 40 በመቶ የሚሆነው የዓለም ኢኮኖሚን የሚሸፍን ነው ያሉት ፕሬዚደንቱ፤ ብሕዝብ ቁጥርም የብሪክስ ቡድን ግማሹን የዓለም ሕዝብ ቁጥር የያዘ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የብሪክስ አባል ሀገራት ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ዋጋ መጠን ከ37 ትሪሊዮን ዶላር በላይ መሆኑንም ጠቁመው ይህ እንደ ቡድን 7 ካሉ ትብብሮች በላይም ጠንካራ እንደሆነ ማሳያ ነው ብለዋል።

የአንድ መንግስት ውግንና እንዲሁም ግንኙነት አሁን ላይ ታሪክ ሆኗል ወደ ባለብዙ ወዳጅነት ምዕራፍም ተሸጋግረናል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ለዚህም ማሳያው ብሪክስ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *