ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር 55 ዓመታትን ባስቆጠረው የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ።
ግንኙነታቸው በሁኔታዎች ሁሉ እንደማይቀያየር አጋሮች፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት የሁለቱ ሀገራት ትብብር ጉልህ ፍሬዎችን ማፍራቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል።
ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን እና አይሲቲን ባካተቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዓምዶች ላይ የሚደረገው ትኩረት እንዳለ ሆኖ፤ ሌሎች የትብብር መስኮችን ለማጠናከርና እንደ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ ሎጂስቲክስ እና ንጹሕ የኃይል ምንጮች ልማት ላይ ያለንን ዕምቅ ዐቅም ለመመልከትም ችለናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።


