በ 15 ዓመታት የለንደን ቆይታዬ የቀሰምኩትን እውቀትና ልምድ ተጠቅሜ ማህበረሰቤን ለማገልገል ዝግጁ ነኝ”

አራተኛው ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት ከሀምሌ 21 እስከ ሀምሌ 25/2017 ዓ.ም “ናፍቆት ድሬ ለድሬዳዋ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል።

በዚህም በበዓሉ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመሳተፍ ከ 15 አመታት የለንደን ቆይታ በኋላ ወደ ትውልድ ሀገሩ ድሬዳዋ የመጣው ወጣት አርተን በበዓሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊሳተፍ በመሆኑ የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ ገልጿል።

ወጣት አርተን ትውልድና እድገቱ ድሬዳዋ ሲሆን ትምህርቱን ከ1ኛ እስከ 10ኛ ክፍል ኖትሮዳም ት/ቤት፤ 11ኛ እና 12ኛ ክፍልን ደግሞ ድሬዳዋ ሀይስኩል ተከታትሎ ወደ ለንደን በማቅናት የቢዝነስ ማኔጅመን ትምህርቱን ተከታትሎ አሁን ላይ በዘርፉ እየሰራም ይገኛል።

ወጣት አርተን ተማሪ እያለሁ የማደርጋቸው የድሬዳዋ ትዝታዎቼ በለንደን በቆየሁባቸው 15 ዓመታት አልተረሱኝም በማለት የሚናገር ሲሆን፤ ድሬዳዋ በአሁኑ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገች እንደምትገኝ መመልከቱን ገልፆ በቀጣይም ይሄ እድገቷ እንዲቀጥል እኔም የበኩሌን አሻራ ማኖር እፈልጋለሁ በማለት ይናገራል።

ወጣቱ በተማርኩበትና እየሰራሁበት በምገኝበት የቢዝነስ ማኔጅመን ሙያ ተሰማርቼ ማህበረሰቤን ለመጥቀም ዝግጁ ነኝ ሲልም አመላክቷል።

በመጨረሻም ወጣቱ በመላው አለም ለሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆች፣ ወዳጆችና ደጋፊዎች ድሬዳዋን ለማሳደግ እንሰባሰብ ሲል ጥሪውን አቅርቧል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *